ከፍተኛ ሊግ | ባህርዳር መሪውን ሲጠጋ ጅማ ከተማ የምድብ ለ መሪነቱን አጠናክሯል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ሲደረጉ ጅማ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ፣ ባህርዳር ከተማ መሪዎቹን የተጠጋበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡

ምድብ ሀ

መሪው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናገደው ቡራዩ ከተማ አቻ ተለያይቷል፡፡ ወልዋሎ በከድር ከሀሊ ጎል ቀዳሚ ቢሆንም ቡራዩ በቀድሞው የአአ ከተማ አጥቂ ፍፁም ካርታ አማካይነት አቻ መሆን ችሏል። በግሩም አጀማመር ምድቡን በርቀት ሲመራ የቆየው ወልዋሎ ባለፉት 4 ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ማድረግ ተስኖት ከተከታዮቹ ያለው ርቀት እየጠበበ ይገኛል፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በሌላ ከተማ እንዲያደርግ የተጣለበት ቅጣት በመነሳቱ አራዳ ክፍለ ከተማን ባህርዳር አፄ ቴዎድሮስ ላይ አስተናግዶ በቀላሉ 3-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ባህርዳር ድሉን ተከትሎ ነጥቡን 23 በማድረስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከወልዋሎ በ8 ነጥቦች ርቆ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በምድቡ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቀለ ከተማ ከ ሱሉልታ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ ሱሉልተታ ከተማዎች ባለመገኘታቸው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ከመተላለፉ ውጪ ይፋ ያደረገው ነገር የለም፡፡

በሌሎች የምድቡ ጨዋታዎች ኮምቦልቻ ላይ ወሎ ኮምቦልቻ አአ ፖሊስን ፣ ባህርዳር ላይ አማራ ውሃ ስራ አክሱም ከተማን በተመሳሳይ 1-0 ሲረቱ ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን ከለገጣፎ ለገዳዲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

[table id=208 /]

[league_table 18186] 

ምድብ ለ

ባለፈው ሳምንት ያልተጠበቀ ሽንፈት ያስተናገደው መሪው ጅማ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን የ2-1 ድል አርሲ ነገሌ ላይ አስመዝግቧል፡፡ ጅማ ላይ በተደረገው ጨዋታ አስራት እና ተመስገን ገብረኪዳን የባለሜዳዎቹን የድል ግቦች ሲያስቆጥሩ ደረሰ ተሰማ የግብ ልዩነቱን ከማጥበብ ያልዘለለች ግብ ለአርሲ ነገሌ አስቆጥሯል፡፡

ደቡብ ፖሊስ ከተከታታይ ድሎች በኋላ ሽንፈት አስተናግዶ ደረጃውን ወደ 3ኛ አውርዷል፡፡ ወልቂጤ ከተማን ያስተናገደው ደቡብ ፖሊስ ከእረፍት መልስ በተቆጠረ ጎል 1-0 ተሸንፏል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና ነቀምት ከተማን አስተናግዶ 3-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ ከፍ ሲያደርግ ድሬዳዋ ላይ ስልጤ ወራቤን ያስተናገደው ናሽናል ሴሜንት 4-1 በመርታት ደረጃውን ወደ 4ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ጂንካ ከተማ ካፋ ቡናን 1-0 ሲረታ ዲላ ከተማ ከ ሻሸመኔ ከተማ 2-2 ተለያይተዋል፡፡ ወደ ነገሌ ቦረና ያቀናው ድሬዳዋ ፖሊስ ደግሞ ከነገሌ ቦረና ያለ ግብ አቻ ቢለያይም ባገኛት 1 ነጥብ ታግዞ ለረጅም ሳምንታት የቆየበትን የሰንጠረዡ ግርጌ ለነቀምት ከተማ አስረክቧል፡፡

[table id=210 /]

[league_table 18205]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *