ዝውውር | ግርማ በቀለ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል

ከሀዋሳ ከተማ ጋር የተለያየው ግርማ በቀለ ማረፊያውን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አድርጓል፡፡ ባንክ ግርማን ያስፈረመው ለ1 አመት ከ6 ወራት በሚቆይ ውል ነው፡፡

ግርማ ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ ከተማ የዲሲፕሊን ቅጣት ተላልፎበት የነበረ ሲሆን ወደፈለገበት ክለብ እንዲጓዝ ከክለቡ ጋር ስምምነት አድርጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡  ስሙ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ዝውውር ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በመጨረሻ ወደ ባንክ መጓዝን ምርጫው አድርጓል፡፡

በመጪው እሁድ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ግርማ በቀለ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ይገጥማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በፕረምየር ሊጉ በርካታ ግቦች በማስተናገድ ቀዳሚ የሆነው እና በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጫዋቾች ዝውውር ራሱን እያጠናከረ ይገኛል፡፡ ግርማ በቀለም ከጥላሁን ወልዴ ፣ አቢኮይ ሻኪሩ ፣ ደረጄ መንግስቱ እና ሮቤል ግርማ በመቀጠል በዚህ የዝውውር መስኮት ወደ ክለቡ የተዛወረ 5ኛው ተጫዋች ያደርገዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *