የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 14ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ ተጠናቋል፡፡ ሀላባ ከተማን ያስተናገደው ፌዴራል ፖሊስም 2-0 ከመመራት ተነስቶ አቻ መለያየት ችሏል፡፡
ከቡድናቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ በመጡ የሀላባ ደጋፊዎች ደምቆ በዋለው ጨዋታ የመጀመርያው አጋማሽ ሀላባ ከተማ በተጋጣሚው ላይ ብልጫ መውሰድ ችሎ ነበር፡፡ በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች በከዩብ በቀታ አማካኝነት ሁለት አስደንጋጭ ሙከራዎች ያደረጉ ሲሆን በ11ኛው ደቂቃ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ተጠቅሞ ግብ አዳኙ ዘካርያስ ፍቅሬ ሀላባን ቀዳሚ አድርጓል፡፡ ከጎሉ በኋላም ጫናቸውን አጠናክረው የቀጠሉት ሀላባዎች ከ5 ደቂቃ በኋላ ዘካርያስ በድጋሚ ባስቆጠረው ጎል መሪነታቸውን ወደ 2-0 ማስፋት ችሏል፡፡
የጨዋታው ደቂቃ እየገፋ በመጣ ቁጥር ሀላባ ጨዋታውን በጀመረበት ፍጥነት መቀጠል ሳይችል ቀርቷል፡፡ ይልቁንም በትኩረት ማጣት የኋላ ኋላ ነጥብ ለመጋራት ተገደዋል፡፡
በ32ኛው ደቂቃ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የዋለው አማካዩ ባህሩ ብድር ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ በግሩም ሁኔታ አርፎ በሀላባ 2-1 መሪነት የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ፌዴራል ፖሊስ የአቻነት ጎል ፍለጋ ተጭኖ ሲጫወት ሀላባ ከተማ በመልሶ ማጥቃት ግብ ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን መፍጠር ችሎ ነበር፡፡ በ88ኛው ደቂቃ በሀላባ የግብ ክልል ውስጥ ኳስ በእጅ መነካቱን ተከትሎ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ደጀኔ አምዴ ወደግብነት ቀይሮ ፌዴራል ፖሊስን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ፌዴራል ፖሊስ ወደ 9ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሀላባ ከተማ ወደ መሪዎቹ የመጠጋት እደድሉን አምክኗል፡፡
ምድብ ሀ
[table id=208 /]
[league_table 18186]
ምድብ ለ
[table id=210 /]
[league_table 18205]