አዲስ አበባ ከተማ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር በዛሬው እለት መለያየቱን ተከትሎ የክለቡ የሴት ቡድን አሰልጣኝ አስራት አባተን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
አስራት አባተ በዘንድሮው አመት የተቋቋመው የአአ ከተማ ሴቶች ቡድንን ሲያሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን የክለቡ ቦርድ ከ08:00 ጀምሮ ስብሰባ በማድረግ አሰልጣኙ የወንዶች ቡድንን እንዲመሩ ከውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡ የስዩም ከበደ ረዳት ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አሰልጣኝ በፀሎት የአስራት ረዳት ሆነው እንደሚቀጥሉም ታውቋል፡፡
ለረጅም ጊዜያት በሴቶች እግርኳስ ላይ በመስራት የሚታወቁት አሰልጣኝ አስራት ከዚህ ቀደም ደደቢት ፣ የኢትዮጵያ ከ20 እና ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድንን መምራታቸው ይታወሳል፡፡