የ2017 ካፍ ከንፌድሬሽን ዋንጫ የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ ሶስት ጨዋታዎች ይጀመራሉ፡፡ ወደ ሁለተኛ ዙር ለማምራት የሚደረጉ ፍልሚያዎች ከወዲሁ ተጠባቂ ናቸው፡፡
የግብፁ ሰሞሃ የኬንያውን ኡሊንዚ ስታርስን ያስተናግዳል፡፡ በግብፅ ፕሪምየር ሊግ የተዘበራረቀ የውድድር ግዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ሰሞሃ ከምስራቅ አፍሪካ ተጋጣሚው የተሻለ የተጫዋቾች ጥራት ስብስብ መያዙ ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡ የኬንያ ጦር ቡድን የሆነው ኡሊንዚ በቅድመ ማጣሪያ ዙር የሰሜን አፍሪካ ክለብን መጣሉ ለሰሞሃው ጨዋታ ያልተጠበቀ አሸናፊ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡
የ2016 ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው ዜስኮ ዩናይትድ የብሩንዲውን ሜሴጀር ደ ንጎዚን በሜዳው ይገጥማል፡፡ ዜስኮ የዛማቢያ ሊግ ዋንጫን ለተቀናቃኙ ዛናኮ አሳልፎ በመስጠቱ በአሁን የውድድር ዘመን ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወርዷል፡፡ የንዶላው ክለብ ዜስኮ አምና በአህጉሪቱ ታላቅ ውድድር ተሳትፎ ሲያደርግ የነበረው ቡድኑን አሁን ላይም መያዙ በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሰፊ ርቀት ሊያስኬደው ይላል፡፡ ተጋጣሚው ሜሴጀር ደ ንጎዚ በውድድሩ የካበተ ልምድ የሌለው መሆኑ በጨዋታው ላይ እንዳይቸገር ተሰግቷል፡፡
የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር በሜዳው የዲ.ሪ. ኮንጎውን ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎን ያስተናግዳል፡፡ ሃያሉ የአልጄሪያ መዲና ክለብ ዳግም ወደ አፍሪካ ክለቦች ውድድር ከተመለሰ ወዲህ በቅድመ ማጣሪያ የጋናውን ቤቸም ዩናይትድ ሲጥል ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ የጋቦኑን አካንዳን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ከተመሰረተ ጥቂት አመታትን ያስቆጠረው የኮንጎው ክለብ ኤምሲ አልጀርን ማሸነፍ ከቻለ ምንአልባትም በዘንድሮው የአፍሪካ ክለቦች ከተመዘገቡት ውጤቶች መካከል አስገራሚው ሊሆን ይችላል፡፡ በአልጄሪያ ሊግ 1 መልካም የሚባል የውድድር ዘመንን እያሳለፈ የሚገኘው ኤምሲ አልጀር የማለፍ ሰፊ ቅድመ ግምትን አግኝቷል፡፡
አርብ
16፡00 – ሰሞሃ (ግብፅ) ከ ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ)
17፡00 – ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) ከ ለ ሜሰጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ)
20፡45 – ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) ከ ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)
ቅዳሜ
15፡00 – ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) ከ ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ)
15፡30 – ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን)
15፡30 – ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ)
16፡00 – ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) ከ ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ)
16፡30 – ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) ከ ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ)
17፡00 – ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) ከ ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)
18፡00 – ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) ከ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን)
እሁድ
16፡00 – ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) ከ ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን)
16፡00 – አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) ከ አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን)
17፡00 – ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) ከ አለ መስሪ (ግብፅ)
19፡00 – መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) ከ ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)
19፡15 – አዛም (ታንዛኒያ) ከ ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)
19፡30 – ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) ከ ስፑርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)