የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀን እና ቦታ ላይ ሽግሽግ ተደርጓል፡፡ የአበበ ቢቂላ ስታድየም ለእድሳት መዘጋት እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የቻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታም ለሽግሽጎቹ ምክንያት ሆነዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ቅዳሜ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ወደ ሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2009 ተሸጋግሯል፡፡ 11:30 ላይም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ቅዳሜ ሊደረግ የነበረው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ደግሞ ሰኞ መጋቢት 11 በአዲስ አበባ ስታድየም 09:00 ላይ ይካሄዳል፡፡
ቅዳሜ 10:00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ አበበ ቢቂላ ስታድየም ለእድሳት በመዘጋቱ ወደ አርብ መጋቢት 8 ተሸጋግሯል፡፡ ጨዋታውም በአዲስ አበባ ስታድየም 10፡00 ላይ ይደረጋል፡፡
የ19ኛ ሳምንት ፕሮግራም
አርብ መጋቢት 8 ቀን 2009
10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)
እሁድ መጋቢት 10 ቀን 2009
09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት (ሀዋሳ)
09:00 ጅማ አባ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ (ጅማ)
09:00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ሶዶ)
09:00 ወልድያ ከ መከላከያ (ወልድያ)
ሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2009
09:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)
11:30 አዲስ አበባ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (አአ ስታድየም)
ለሌላ ጊዜ የተላለፈ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከተማ