ኮንፌድሬሽን ዋንጫ፡ ዜስኮ፣ ሰሞሃ እና ሴፋክሲየን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል

ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወደ መጨረሻ ዙር ለማለፍ የሚደረጉ ትንቅንቆች ቅዳሜ ቀጥለዋል፡፡ ዜስኮ ዩናይትድ፣ ሰሞሃ፣ ሴፋክሲየን፣ ኢትሃድ ታንገር፣ ፕላቲኒየም ስታርስ እና ጄኤስ ካቤሌ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ማለፍ የቻሉበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ወደ ሃራሬ ያቀናው የአንጎላው ሬክሬቲቮ ሊቦሎ ከንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ ጋር ያለግብ አቻ ተለያይቶ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡ ባለሜዳዎቹ በጨዋታው በከፍተኛ ሁኔታ እድሎችን ሲያመክኑ የነበረ ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዘር ማለፍ የሚችሉበትን እድል ከእጅቻው ላይ አጥተዋል፡፡

የኬንያው ኡሊንዚ ስታርስ የግብፁን ሰሞሃን 3-0 ቢያሸንፍም ከኮንፌድሬሽን ዋንጫው በድምር ውጤት ተሸንፎ ወድቋል፡፡ ኡሊንዚ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ግዜ በ10 ተጫዋች ለመጫወት የተገደደ ሲሆን በጨዋታውም ከተጋጣሚው በእጅጉ ልቆ ተገኝቷል፡፡ ሳሙኤል ኦኒያንጎ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ኦማር ምቦንጊ ቀሪዋን አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የደቡብ አፍሪካው ፕላቲኒየም ስታርስ የዩጋንዳው ቫይፐርስን 3-1 በመርታት ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ አልፏል፡፡ የፕላቲኒየምስ ስታርስን የድል ግቦች መካከል ግብ ጠባቂው ምቦንጌኒ ምዚሜላ በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ሲያስቆጥር ንዱሚሶ ማቤና አንዷን አክሏል፡፡ ሚልተን ካሪሳ የቫይፐርስን ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡

የሞሮኮው ኢትሃድ ታንገር በአህመድ ሃሙዳን ሶስት ግቦች ታግዞ 3-0 የጊኒውን ኤኤስ ካሎምን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻለበትን ውጤት በሜዳው ማሳካት ችሏል፡፡ የአልጄሪያው ጄኤስ ካቤሌ በሜዳው የኮንጎ ሪፐብሊኩን ኤቷል ዱ ኮንጎን 1-0 አሸንፏል፡፡ የካቤሌን ግብ መሃመድ ኤል ሃዲ በቅጣት ምት ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀሩትን አስቆጥሯል፡፡

ፊፋ የማሊ የስፖርት ሚኒስቴር የሃገሪቱን የእግርኳስ ፌድሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላትን ከስልጣን ካነሳ በኃላ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ምክንያት ማሊን ከውድድር ስላገደ የሩዋነዳው ራዮን ስፖርት እና የግብፁ አል መስሪ በፎርፌ አላፊ ቡድኖች ሆነዋል፡፡ የማሊዎቹ ኦንዜ ክሪቸርስ እና ጆሊባ የፊፋ የቅጣት በትር የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ሆነዋል፡፡ ኦንዜ ራዮን ስፖርትን እንዲሁም ጆሊባ አል መስሪን ባማኮ ላይ አሸንፈው ነበር፡፡

 

አርብ ውጤት (በቅንፍ የተጠቀሰው የድምር ውጤት ነው)

ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 2-1 ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) (2-3)

 

ቅዳሜ ውጤቶች

ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ) 0-0 ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) [1-2]

ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን) 1-1 ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) [1-6]

ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ) 3-0 ሰሞሃ (ግብፅ) [3-4]

ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር) 1-0 መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) [2-3]

ለ ሜሰንጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ) 2-2 ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) [2-4]

ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ) 3-0 ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) [3-1] * (ራዮን ስፖርት በፎርፌ አሸናፊ ሆኗል)

ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ) 3-1 ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) [3-1]

ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ) 1-0 ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) [1-0]

አለ መስሪ (ግብፅ) 3-0 ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) [3-2] * (አል መስሪ በፎርፌ አሸናፊ ሆኗል)

ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ) 3-1 ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) [3-2]
እሁድ

14፡30 – ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን) ከ ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) [1-9]

15፡00- አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን) ከ አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) [0-2]

15፡30 – ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) ከ አዛም (ታንዛኒያ) [0-1]

18፡00 – ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ከ ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) [2-3]

20፡00 – አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን) ከ ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [0-1]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *