ቻምፒየንስ ሊግ፡ ሜሪክ፣ ሰንዳውንስ እና ዋይዳድ ወደ ምድብ አልፈዋል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የአንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲጀመር ዛናኮ፣ ኮተን ስፖርት፣ አል አሃሊ ትሪፖሊ፣ ኤል ሜሪክ፣ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ዋይዳድ ካዛብላንካ እና ዩኤስኤም አልጀር ወደ ምድብ የገቡበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ወደ አንታናናሪቮ ተጉዞ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርትን የገጠመው የካሜሮኑ ኮተን ስፖርት አቻ በመለያየት ወደ ምድብ አልፏል፡፡ በሜዳው 1-0 ማሸነፍ የቻለው ኮተን የማዳጋስካሩ ክለብ ጋር 1-1 መለያየቱ ወደ ምድብ እንዲገባ አስችሎታል፡፡

የዛምቢያው ዛናኮ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር ያለግብ አቻ በመለያየት ወደ ምድብ ገብቷል፡፡ ዛናኮ በሁለት ተከታታይ የሜዳው ላይ ጨዋታዎች ግብ ሳያስቆጥር አቻ ቢለያይም ከሜዳው ውጪ ያስመዘገባቸው ወሳኝ ውጤቶች ወደ ምድብ እንዲገባ አድርጎታል፡፡

የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ በጋቦኑ ሞናና በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረበትን ግብ ቢሸነፍም በመለያ ምት 5-4 በማሸነፍ ወደ ምድብ ገብቷል፡፡ የ2016ቱ የቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ በዘንድሮው የአፍሪካ ክለቦች ታላቅ ውድድር በእጅጉ ተዳክሞ ታይቷል፡፡

የዩጋዳው ኬሲሲኤ የወቅቱን ቻምፒዮኑን ማሜሎዲ ሰንዳውንስን ባስተናገደበት ጨዋታ 1-1 ተለያይቷል፡፡ ኬሲሲኤ በአንጋፋው አጥቂ ጂኦፍሪ ሴሬንኩማን አማካኝነት በመጀመሪያው አጋማሽ መሪ ሆኗል፡፡ በሁለተኛው አጋመሽ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው አንቶኒ ላፎር ብራዚሎቹን ወደ ምድብ ያስገባችን እና የአቻነት ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡

ፉስ ራባት ባልተጠበቀ መልኩ በሊቢያው አል አሃሊ ትሪፖሊ ተሸንፎ ከቻምፒየንስ ሊጉ ወጥቷል፡፡ የሞሮኮ ቻምፒዮኑ ፋስ ራባት በሜዳው የትሪፖሊውን ክለብ 3-1 ቢያሸንፍም ከሳምንት በፊት የደረሰበት የ2-0 ሽንፈትን ተከትሎ ከውድድር ወጪ ሆኗል፡፡

ከሳምንት በፊት ፖርት ሃርኮት ላይ የሰረበትን የ3-0 ሽንፈት በመቀልበስ ወደ ምድብ የገባው የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ነው፡፡ ሃያሉ የኦምዱሩማን ክለብ የናይጄሪያውን ሪቨርስ ዩናይትድ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ ባክሪ አል መዲና በመጀመሪያው አጋማሽ ሃት-ትሪክ ሰርቷል፡፡ ሪቨርስ ዩናይትድ ተጫዋቾች አርብ እለት ወደ ልምምድ ሜዳ ሲያመሩ የቡድኑ ባስ በሜሪክ ደጋፊዎች ጥቃት ደርሶበታል፡፡

ተሸናፊዎች ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት፣ ያንግ አፍሪካንስ፣ ሞናና፣ ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ፣ ኬሲሲኤ፣ ፉስ ራባት እና ሪቨርስ ዩናይትድ በኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ቅዳሜ ውጤቶች

ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር) 1-1 ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) [1-2]

ዛናኮ (ዛምቢያ) 0-0 ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) [1-1] (ዛናኮ ከሳምንት በፊት ዳሬ ሰላም ላይ ባስቆጠረው ግብ አሸንፏል)

ሞናና (ጋቦን) 1-0 ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) [1-0] [ዋይዳድ በመለያ ምት 5-4 አሸንፏል]

ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ) 2-1 ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ) [2-3]

ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) 1-1 ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) [2-3]

ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ) 3-1 አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) [3-3] (አሃሊ ትሪፖሊ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አሸንፏል)

ኤል ሜሪክ (ሱዳን) 4-0 ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) [4-3]

 

እሁድ

15:00 – ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [1-1]

15:00 – ኤኤስ ደ ታንዳ (ኮትዲቯር) ከ ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ) [0-3]

15:15 – ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ) ከ አል ሂላል (ሱዳን) [0-3]

15:30 – ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (ጋምቢያ) [1-1]

15:30 – ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ አል አሃሊ (ግብፅ) [0-1]

16:00 – ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ) ከ ክለብ ፌሬቫያሮ ደ ቤይራ (ሞዛምቢክ) [0-2]

16:00- ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) ከ ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሲ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) [1-0]

16:00 – ሆሮያ (ጊኒ) ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) [1-3]

16:00 – ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ዛማሌክ (ግብፅ) [1-4]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *