የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 1ኛ ዙር ግምገማ ዛሬ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን 1ኛ ዙር ባለፈው እሁድ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የግማሽ የውድድር ዘመኑ ግምገማም ዛሬ ከ3:00 ጀምሮ የፌዴሬሽኑ አመራሮች እና የክለብ ሀላፊዎች በተገኙበት በቸርችል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

የአፈጻጸም ግምገማ እና ውይይቱ በፌዴሬሽኑ የብሄራዊ ውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ መሪነት የተካሄደ ሲሆን የአንደኛው ዙር አጠቃላይ የክንውን ሪፖርት በውድድር ማዘውተርያ ስፍራዎች ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ከአቶ ሰለሞን በመቀጠልም የዳኞች ፣ የዲሲፕሊን ፣ የፀጥታ እና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች ሪፖርት በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ቀርቧል፡፡

ከሪፖርት በመቀጠል የክለብ ተወካዮች ለኃላፊዎቹ ያለላቸውን ጥያቄ እና በውደድሩ ላይ ያላቸውን አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

-የዳኞች አመዳደብ እና የውሳኔዎች አሰጣጥ መስተካከል ይኖርበታል

– የክለቡ ሜዳዎች መስተካከል እንዳለበት

– ከክለቦች የሚመጡ የጨዋታ ማራዘም ጥያቄ እንዴት እያስተናገደ ይገኛል?

– በቀጣይ የአበበ ቢቂላ ስታድየምን መዘጋት ተከትሎ የአዲስ አበባ ክለቦች እጣ ፈንታ

– የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም አወጣጥ

– ኮምሽነሮች የሚሰጡት ሪፓርት ታማኝነት ይኑረው

– የቡድኖች እኩል ጨዋታ አለመጀመር

– የአንድ ክለብ መቀጣት በበጀት እየጎዳ ነው፡፡ በየሳምንቱ የሚላከው ኮሚንኬ እንደሚያሳየው ክለቦችን ከፍተኛ ወጪ ላይ እየጣለ ነው፡፡

– በየክልሉ የሚገኙት የፀጥታ ሀይሎች ከፌዴሬሽን ጋር በጋራ ይስሩ የሚሉት እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ከተሰብሳቢዎች ተሰንዝረው የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ለሚመለከተው ጥያቄ በሰጠው ምላሽ ክለቦች እጃቸውን ከዳኞች ላይ መስብሰብ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የውድድር ማዘውተርያዎችን በተመለከተ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ካለው የጨዋታ መደራረብ አንፃር ምንም አይነት ጨዋታ ማስተናገድ እንደማይቸል የተገለፀ ሲሆን ክለቦች የሚጫወቱበትን ሜደዳ የመፈለግ ሀላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የፕሮግራም እኩል ላለመጀመሩ ክለቦች የአንደኛው ዙር ጨዋታቸውን በተመሳሳይ ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ይህን ለማመጣጠን እና ከሰኔ 30 በፊት ውድድር ለማጠናቀቅ በማለም እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአንደኛው ዙር ከፍተኛ ሊጉ እንዲጓተት ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ዋንኛ የሆነው ክለቦች ተጫዋቾች ስለተጎዱብኝ ይራዘምልኝ ጥያቄዎች መበርከታቸው መሆኑ ተገልጾ በሁለተኛው ዙር ግን ከዚህ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ፌዴሬሽኑ እንደማይቀበል አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *