የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል በሚያዚያ ወር ይወጣል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) የቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ዕጣ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኘው የኮንፌድሬሽኑ ዋና ፅህፈት ቤት በሚያዚያ ወር እንደሚያወጣ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ 

ሚያዚያ 18 በሚወጣው የምድብ ድልድል ላይ 16 ቡድኖች በቻምፒየንስ ሊጉ ሲሳተፉ 16 ቡድኖች ደግሞ በኮንፌድሬሽን ዋንጫው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ባሳለፍነው እሁድ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ምድብ ማለፉን ያረጋገጠው የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የምድብ ተጋጣሚዎቹን ለማወቅ እስከሚያዚያ መታገስ ያስፈልገዋል፡፡

በቻምፒየንስ ሊጉ አንደኛ ዙር ተሸንፈው ከምድብ የተሰናበቱ 16 ቡድኖች ወደ ኮፌድሬሽን ዋንጫው ወርደው ከኮንፌድሬሽን ዋንጫ የአንደኛ ዙር አሸናፊዎች ጋር ወደ ምድብ ለመግባት ይፋጠጣሉ፡፡ ካፍ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ በኮንድሬሽን ዋንጫ የምድብ ተፋላሚዎች ከታወቁ ወዲህ በጋራ የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ሲያወጣ ቆይቷል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ የኦምዱሩማን ሃያሎቹ ኤል ሜሪክ እና አል ሂላል በምድብ ድልድል ውስጥ ሲገኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስተኛው ቡድን ነው፡፡ የሃገራት ክለቦች በአምስት ዓመታት በአፍሪካ የክለቦች ውድድር ባመጡት ውጤት መሰረት በአራት ቋት ውስጥ በሳምንቱ መጀመሪያ መመደባቸው ይታወሳል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት ነጥብ በአራተኛው ቋት ላይ ይገኛል፡፡ ፈረሰኞቹ ሁለት ነጥብ ሊያገኙ የቻሉት በ2013 ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የቱኒዚያዎቹ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን፣ ኤቷል ደ ሳህል እና የማሊው ስታደ ማሊያን በተገኙነት ምድብ የምድቡን ግርጌ ይዞ በማጠናቀቁ ነው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተሰላፊ ሳላዲን ሰዒድ በአምስት ግቦች የቻምፒየንስ ሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት ሲመራ አልጄሪያዊው የክለብ አፍሪኬን የመስመር አማካይ ኢብራሂም ቼኒሂ በአራት ግቦች የኮንፌድሬሽን ዋንጫው የግብ አግቢዎች ሰንጠረዥን ይመራል፡፡

 

የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ተሳታፊ ክለቦች

አል አሃሊ እና ዛማሌክ (ግብፅ)፣ ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ)፣ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)፣ አል ሂላል (ሱዳን)፣ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ)፣ ዋይዳድ ክለብ አትሌቲክ (ሞሮኮ)፣ ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ)፣ ኤል ሜሪክ (ሱዳን)፣ ኮተን ስፖርት (ካሜሮን)፣ ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)፣ አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ)፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)፣ ፌሮቫያሪዮ ደ ቤራ (ሞዛምቢክ)፣ ዛናኮ (ዛምቢያ) እና ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ)

 

የኮንፌድሬሽን ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ)

ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ዩኒየስ ስፓርቲፍ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ)

ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሲ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)

ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ) ከ መግረብ ደ ፌስ (ሞሮኮ)

ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ)

ሞናና (ጋቦን) ከ አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር)

ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ) ከ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ)

ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ሰሞሃ (ግብፅ)

ስናፕስ ስፓርትስ (ማዳጋስካር) ከ ሬክሬቲቮ ዴስፖርቲቮ ደ ሊቦሎ (አንጎላ)

ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቶ (ዩጋንዳ) ከ አል መስሪ (ግብፅ)

ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (ጋምቢያ) ከ አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን)

ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ ከ ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ)

ሪቨርስ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ)

ባራክ ያንግ ኮንትሮለርስ (ላይቤሪያ) ከ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)

ኤኤስ ታንዳ (ኮትዲቯር) ከ ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ)

ሆሮያ (ጊኒ) ከ ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *