መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 2ኛ   መከላከያ   2- 1  ቅዱስ ጊዮርጊስ  

52′ አብዱልከሪም ኒኪማ 58′ አዲስ ተስፋዬ           62’ሳሙኤል ሳሊሶ

91′ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ብሩኖ ኮኒ ግብ ቢያስቆጥርም ዳኛው ከጨዋታ ውጪ በሚል ሽረውታል፡፡

90′ አራተኛ ዳኛው ተጨማሪ 5 ደቂቃ አሳይቷል፡፡

88′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች የአቻነቷን ግብ ለማስቆጠር ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛል፡፡

86′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ 

ግብጠባቂው አቤል ማሞ ባጋጠመው ጉዳት በይድነቃቸው ኪዳኔ ተተክቷል

82′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዳነ ግርማ ወጥቶ ብሩኖ ኮኔ ገብቷል 

82‘ የመከላከያው ግብጠባቂ አቤል ማሞ ተጎድቻለው በሚል በሜዳ ውስጥ ተኝቶ ይገኛል፡፡

81′ ቢጫ ካርድ

ምንይሉ ወንድሙ ሰአት በማባከን ቢጫ ካርድ ተመልክቷል 

80′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ 

ሳሙኤል ታዬ ወጥቶ ኦጎታ ኦዶክ ገብቷል 

75′ በስታዲየሙ እየጣለ በሚገኘው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ ሁለቱም ቡድኖች በመጠኑም ቢሆን መቀዛቀዝ ታይቶበታል ፤ ሁለቱም ቡድኖች በኩል በረጃጅሙ በሚጠለዙ ኳሶች በርከት ብለዋል፡፡

72′ በተለምዶ ካታንጋ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የሚገኙት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ከባድ ዝናቡም ሳይበግራቸው ለክለባቸው አለኝታ መሆናቸውን እያሳዩ ይገኛል፡፡

70′ ጨዋታው በከባድ ዝናብ ታጅቦ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

65′ ከግቧ መቆጠር በኃላ መከላከያዎች በቀጥተኛ አጨዋወት ኳሶችን በተደጋጋሚ ለምንይሉ ወንድሙ በማድረስ የምንይሉን አስደናቂ ፍጥነት በመጠቀም ተጨማሪ ግቦችን ለማስቆጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡

62′ ጎል መከላከያ 

ሳሙኤል ሳሊሶ ከመሀል ሜዳ በግሩም ሆኒታ የተሻገረለትን ኳስ የዘሪሁን ታደለን መውጣት ተመልክቶ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡

58′ ጎል መከላከያ 

ሚካኤል ደስታ ያሻማውን የማእዘን ሆኒታ አዲሱ ተስፋዬ በግሩም ሆኒታ ገጭቶ አስቆጥሯል 

58′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ 

ማራኪ ወርቁ ወጥቶ ባዬ ገዛኸኝ ገብቷል

57′ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !!!
ሳሙኤል ታዬ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ክልል ውጪ የመታውን ኳስ ዘሪሁን ታደለ በአስደናቂ ሆኒታ አድኖበታል፡፡

 52′ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ 

በሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ ተቀይሮ የገባው አብዱልከሪም ኒኪማ በግራ መስመር ከአበባው ቡጣቆ የተቀበለውን ኳስ ከመከላከያ የግብ ክልል ውጪ አክርሮ በመምታት ግሩም ግብ አስቆጥሯል፡፡

48′ ቢጫ ካርድ

አበባው ቡጣቆ ከሽመልስ ተገኝ ጋር በፈጠረው ሰጣ ገባ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

46′ የሁለተኛው አጋማሽ በመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ አማካይነት ተጀምሯል፡፡

የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፕሪንስ ሲቨሬን ወጥቶ አብዱልከሪም ኒኪማ ገብቷል

የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ አራተኛው ዳኛ ተጨማሪ 4 ደቂቃ አሳይተዋል 

41′ የሚያስቆጭ አጋጣሚ 

አብበከር ሳኒ ከማእዘን ምት ያገኘውን ፍፁም ግልፅ የሆነ የማግባት አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

36′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቀጥተኛ አጨዋወት ወደ መከላከያ የግብ ክልል በሁለት ተከታታይ አጋጣሚዎች መድረስ ቢችሉም የመከላከያ ተከላካዮች የሚቀመሱ አልሆኑም፡፡

32′ የመከላከያ የመስመር ተከላካዮች በተለይም ሽመልስ ተገኝ ተገማች የሆነው የጊዮርጊስን የመስመር አጨዋወት በመግታት በኩል የተዋጣለቸው ሆነዋል፡፡

31’ቢጫ ካርድ

ሚካኤል ደስታ ናትናኤል ዘለቀ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል

27′ ቢጫ ካርድ

ሽመልስ ተገኝ ኳስ በእጅ በመንካቱ የተነሳ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

27′ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !!!

አቡበከር ሳኒ ከመስመር ያሻማውን ኳስ በመከላከያ የግብ ክልል ውስጥ ይገኝ የነበረው ምንተስኖት አዳነ ኳሷን ተቆጣጥሮ ወደ ግብ ለመሞከር ጥረት ሲያደርግ ሽመልስ ተገኝ ኳስ በእጅ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት አዳነ ግርማ ቢመታም አቤል ማሞ ሊያድንበት ችሏል፡፡

20′ መከላከያዎች ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተሻለ መልኩ በተደጋጋሚ ወደፊት በመድረስ የግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡

18′ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !!!

መከላከያዎች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ያገኙትን ኳስ ሳሙኤል ሳሊሶ ከዘሪሁን ታደለ ጋር 1ለ1 ቢገናኝም ኳሳን ሳይጠቀምባት ቀርቷል 

16′ በዛሬው ጨዋታ ላይ ሁለቱ የመከላከያ የመስመር ተከላካዮች እንቅስቃሴ በተለይም የማጥቃት እንቅስቃሴነውን በማገዝ በኩል ተገድቦ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

14′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከወትሮው በተለየ ይህ ነው የሚባል የግብ እድልን ለመፍጠር አልቻሉም፡፡

11′ መከላከያዎች ፊት ላይ የሚገኙትን ተጫዋቾቹን ፍጥነት በመጠቀም በመልሶ ማጥቃት በቶሎ ቶሎ ወደ ፊት ለመሄድ ጥረት ቢያደርጉም በተደጋጋሚ በቀላሉ ኳሶቹ ወደ ማጥቃት ክልል ሲደርሱ እየተበላሸባቸው ይገኛል፡፡

6′ የጨዋታውን የመጀመሪያውን ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ መከላከያዎች ከቋመ ኳስ በቀጥታ ሳሙኤል ሳሊሶ ቢሞክርም የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብጠባቂ ዘሪሁን ታደለ አድኖበታል፡፡
2′ በጨዋታው ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ማርት ኖይ ባለቤታቸው የጤና እክል ስለገጠማቸው በዚህም የተነሳ ወደ ሆላንድ በማናተቸው በዛሬው ጨዋታ ላይ ረዳቶቻቸው ፋሲል እና ዘሪሁን በጋራ ቡድኑን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

1′ ጨዋታው በሰልሀዲን ሰኢድ አማካኝነት በቅዱስ ጊዮርጊሶች ተጀምሯል፡፡

11:16 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ልምምዳቸውን ጨርሰው ወደ መልበሻ ቤት አቅንተዋል፡፡
11:01 የሁለቱ ቡድኖች ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡


የሁሉቱ ቡድኖች ቋሚ ተሰላፊዎች ይህንን ይመስላል፡፡

መከላከያ 

1   አቤል ማሞ

3 ቴዎድሮስ በቀለ-16 አዲስ ተስፋዬ-4 አወል አብደላ-2 ሽመልስ ተገኝ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ-21 በሀይሉ ግርማ-13 ሚካኤል ደስታ-19 ሳሙኤል ታዬ

7 ማራኪ ወርቁ-14 ምንይሉ ወንድሙ

ተጠባባቂዎች

30 ይድነቃቸው ኪዳኔ

12 ምንተስኖት ከበደ

28 ሚሊዮን በየነ

26 ኦጉታ ኦዶክ

15 ቴዎድሮስ ታፈሰ 

17 ባየ ገዛኸኝ 

10 የተሻ ግዛው

ቅዱስ ጊዮርጊስ
12 ዘሪሁን ታደለ

2 ፍሬዘር ካሳ- 13 ሰልሀዲን በርጌቾ-15 አስቻለው ታመነ-4 አበባው ቡጣቆ
19- አዳነ ግርማ-26 ናትናኤል ዘለቀ-23 ምንተስኖት አዳነ

18 አቡበከር ሳኒ-7 ሰልሀዲን ሰኢድ-11 ፕሪንስ ሴቨሪን

ተጠባባቂዎች

1 ፍሬው ጌታሁን

12 ደጉ ደበበ

21 ተስፋዬ አለባቸው

27 ከሪም ኒኪማ

17 ብሩኖ ኮኔ

3 መሀሪ መና

25 አንዳርጋቸው ይላቅ

ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን የዛሬውን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ይመራል፡፡



ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን! 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ ሶከር ኢትዮጵያ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *