የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ አቻው በሜዳው ተሸንፏል፡፡ በቅድመ ማጣርያው ሲሸልስን በደርሶ መልሱ 5-0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈው ወጣት ቡድን ብዙ ቢጠበቅም በገዛ ሜዳው ደቡብ አፍሪካን መቋቋም ተስኖታል፡፡ ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአላስፈላጊ ቅብብሎች እና ባልተደራጀ አጨዋወት ሲቸገር የነበረው ወጣት ቡድኑ የመጀመርያውን አጋማሽ ካለግብ 0-0 አጠናቋል፡፡ ለዚህም የግብ ጠባቂው አሰግድ አስተዋፅኦ የጎላ ነበር፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ የተለየ ለውጥ ያላሳየው ወጣት ቡድኑ 2 ግቦችን አስተናግዶ በሜዳው ማግኘት የነበረበትን እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
በመልሱ ጨዋታ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ በሜዳው ያስመዘገበውን ውጤት የመቀልበስ እጅግ አስቸጋሪ ፈተና ይገጥመዋል፡፡
{jcomments on}