ቅዱስ ጊዮርጊስ ለቻምፒዮንነት ተጠግቷል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት በጉጉት ሲጠበቅ የሰነበተው የኢትዮጵያ ቡና እናየ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በ,ፈረሰኞቹ የበላይነት ተጠናቋል፡፡

በመሃከላቸው የ13 ነጥብ መሪነት ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በፍፁም ገብረ ማርያም ግብ 1-0 መርተው ለእረፍት ሲወጡ በሁለተኛው አጋማሽ 52ኛ ደቂቃ ላይ ዳዊት እስጢፋኖስ ኢትዮጵ ቡናን አቻ አድርጓል፡፡ በሁለተኛው ዙር አስደናቂ አቋም ይዞ ብቅ ያለው ፍፁም ገብረ ማርያም ኢትዮጵያ ቡናዎች አቻ የምታደርጋቸውን ግብ አስቆጥረው ብዙም ሳይቆዩ በ56ኛው ደቂቃ ቅዱስ ጊዮርጊስን ወደ መሪነት መልሶታል፡፡ ጨዋታውም በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቆ በመሃላቸው የነበረው የነጥብ ልዩነት ወደ 16 ከፍ ብሏል፡፡

ከ19 ጨዋታዎች 18ቱን አሸንፎ የደረጃ ሰንጠረዡን ብቻቸውን እየጋለቡ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በዚህ አካሄዳቸው በቀጣዮቹ ጨዋታዎች የዋንጫ ባለቤትነታቸውን ቀድመው የማረጋገጣቸው ነገር አይቀሬ ነው፡፡

ቅዳሜ በአበበ ቢቂላ በተካሄደ ብቸኛ ጨዋታ መከላከያ ኢትዮጵያ መድንን 1-0 አሸንፏል፡፡ ለጦሩ ብቸኛዋን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው በቅርቡ ከጉዳነቱ የተመለሰው ተክለወልድ ፍቃዱ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ነው፡፡ ድሉን ተከትሎ መከላከያ በ28 ነጥብ 3ኛ ደረጃውን ከሲዳማ ቡና ተረክቧል፡፡

ሌሎች የ19ኛ ሳምንት ጨዋዎች በኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ሰበብ ወዳልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *