የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ረቡዕ በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ሲደረጉ መሪው ጅማ ከተማን ጨምሮ አናት ላይ የሚገኙ ክለቦች ነጥብ ጥለዋል፡፡ ሀላባ ከተማ ደግሞ አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡
ዲላ ላይ ጅማ ከተማን ያስተናገደው ዲላ ከተማ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በሁለተኛው ዙር መልካም ጉዞ እደረገ የነበረው ጅማ ከተማ የተከታዮቹን ነጥብ መጣል ተከትሎ ልዩነቱን የማስፋት እድሉን አምክኗል፡፡
ተከታዩ ወልቂጤ ከተማ ወደ ጅንካ አቅንቶ ድል ሳይቀናው ተመልሶል፡፡ ጅንካ ከተማዎች ከዕረፍት በፊት እና በኋላ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2-0 አሸንፈው መውጣት ችለዋል፡፡ ሶስተኛ ላይ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕናም ድሬዳዋ ፖሊስን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡
ሻሸመኔ ከተማን ያስተናገደው ሀላባ ከተማ 2-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ና ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡ የከፍተኛ ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ የሚገኘው ዘካርያስ ፍቅሬ እና ተመስገን የሀላባን ጎሎችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ቦንጋ ላይ ካፋ ቡናን ከ ደቡብ ፖሊስ ያገናኘው ጨዋታ እስከ ጨዋታው መገባደጃ ድረስ ካፋ ቡና 1-0 ሲመራ ቆይቶ በተጨማሪ ደቂቃ ደቡብ ፖሊሶች ባስቆጠሩት ግብ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡ ነቀምት ላይ ነቀምት ከ ስልጤ ወራቤ ያገናኘው ጨዋታም ሌላው በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ጨዋታ ነበር፡፤
ድሬዳዋ ላይ ነገሌ ቦረናን ያስተናገደው ናሽናል ሴሜንት 1-0 ሲሸነፍ አዲስ አበባ ላይ ፌደራል ፖሊስ አርሲ ነገሌን 1-0 አሸንፏል፡፡