የ2017 የኮፓ ኮካ ኮላ የትምህርት ቤቶች ውድድር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በከፊል ተጀምሯል፡፡
የአፋር ክልል መጋቢት 30 ላይ የመክፈቻ ስነስርአት የተደረገ ሲሆን በእለቱም ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ የጋምቤላ እና የኢትዮ ሶማሌ ክልሎችም ውድድራቸውን መጀመር ችለዋል፡፡
እንደ አፋር ሁሉ በተመሳሳይ ሳምንት የሐረሪ ክልል የትምህርት ቤቶች ውድድር በአሚር ሀቦባ ሜዳ የመክፈቻ ስነስርአት እና ጨዋታዎች ሲካሄዱ በዚህ ሳምንት መጨረሻም 2ኛ ጨዋታቸውን በጁንየር ሜዳ ያደርጋሉ፡፡
በኦሮምያ ክልል የተወሰኑ ዞኖች ውድድሮች ተጀምረዋል፡፡ አርብ ሚያዝያ 6 ጅማ ላይ የትምህርት ቤቶች የውስጥ ውድድር የተጀመረ ሲሆን በቅርቡም የእርስ በእርስ የትምህርት ቤቶች ውደድድር ይጀመራል ተብሏል፡፡ ማክሰኞ ሚያዝያ 10 የሆለታ ፣ ሚያዝያ 11 የባቱ ውደድር ሲጀመር የሰበታ ውድድር ደግሞ ዛሬ የሚጀመር ይሆናል፡፡
የአማራ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ትግራይ እና ድሬዳዋ ውድድሮች በዚህ ሳምንት ይጀምራሉ ተብሎ ሲጠበቅ የደቡብ እና አዲስ አበባ ውድድሮች እጣ ፈንታ አልታወቀም፡፡
የ2017 የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች ውድድር የትምህርት ቤቶች ውድድርን ካካሄደ በኋላ የክልል አቀፍ ውድድር ተካሂዶ ምርጥ ብቃታቸውን የሚያሳዩ ተጫዋቾች ክልላቸውን በመወከል ክረምት ላይ በተመረጠ ከተማ ሀገር አቀፍ ውድድር ያካሂዳሉ፡፡
*ሶከር ኢትዮጵያ የውድድሩን ሁኔታ በደጊዜው እየተከታተለች ለአንባቢዎች መረጃዎች የምታደርስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡