የኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ሆሮያን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጀመራል

የደቡብ አፍሪካው ሱፐርስፖርት ዩናይትድ በሜዳ የጊኒውን ሆሮያን የሚገጥምበት ጨዋታ የ2017 ካፍ ቶታል ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምደብ መክፈቻ ጨዋታ ይሆናል፡፡ፕሪቶሪያ ላይ በሚደረገው ጨዋታ በምደብ መ የሚገኙትን ሁለቱ ክለቦች ያገናኛል፡፡

ሱፐርስፖርት በያዝነው ሳምንት በሊግ ጨዋታ ለዋንጫ የሚፎካከረውን ኬፕታውን ሲቲን 4-2 ያሸነፈ ሲሆን በጥሩ መነቃቃትም የኮናክሬውን ክለብ ለመግጠም ተዘጋጅቷል፡፡ ምድቡ ውስጥ ሃያሉ እና የወቅቱ ቻምፒዮን ቲፒ ማዜምቤ መገኘቱ ቀሪዎቹ ሶስት ክለቦች ቢያንስ በሜዳቸው እና እርስበእርስ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይ ነጥብ እንዲሰበስቡ ያስገድዳቸዋል፡፡

በጊኒ ሊግ 1 ኒምባ ማይኒንግ የአምና አናት ላይ የተቀመጠው ሆሮያ በቻምፒየንስ ሊግ እንደተጋጣሚው ሁሉ የምድብ ጨዋታዎች ልምድ የለውም፡፡ ቢሆንም ሆሮያ ከሜዳው ውጪም ክለቦች የመፈተን ሃይል አለው፡፡ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ በአብሳ ፕሪምየርሺፕ በ48 ነጥቦች አራተኛ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *