ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT |  ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ

______________

 

ተጠናቀቀ!

ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተፈጽሟል፡፡

 

ቢጫ ካርድ

90+1′ አዳነ ግርማ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

 

90′ አብዱልከሪም ንኪማ ከግራ መስመር ወደ ውስጥ በመግባት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ቤነን ሸሪፍያ በእግሮቹ አውጥቶታል፡፡

 

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

 

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

84′ ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ ተስፋዬ አለባቸው ገብቷል፡፡

 

82′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ታሀ ያሲን ቢያስቆጥርም በእጁ ተጠቅሞ ነው በሚል ሳይጸድቅ ቀርቷል፡፡ ታሀ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

 

ቢጫ ካርድ

81′ አስቻለው ታመነ የማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

 

የተጫዋች ለውጥ

80′ ፕሪንስ ሰቨሪንሆ ወጥቶ አቡበከር ሳኒ ገብቷል፡፡

 

72′ ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ኳስ ፕሪንስ በቮሊ ሞክሮ ግብ ጠባቂው ሲያወጣበት ሳላዲን አግኝቶ ሞክሮ በድጋሚ ግብ ጠባቂው መልሶበታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ሳላዲን መትቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

 

67′ አኔስ ባድሪ ያሻማውን ኳስ ታሀ ያሲን በግምባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

 

ቀይ ካርድ!

64′ ጋሌኒ ቻላሊ በፕሪንስ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

 

61′ አብዱልከሪም ንኪማ ከርቀት በቀኝ እግሩ አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

 

የተጫዋች ለውጥ – ኤስፔራንስ

56′ ኤደም ርጃይቢ ወጥቶ አኔስ ባደድሪ ገብቷል፡፡

 

52′ አብዱልከሪም ኒኪማ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመቅረብ ረገድ የተሻለ ሆኗል፡፡

 

49′ ሳላዲን በግሩም የማጥቃት እንቅስቃሴ ወደ ግብ ክልል ተጠግቶ ለአዳነ ያመቻቸለትን ኳስ አዳነ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

 

ተጀመረ!

2ኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

 

እረፍት

የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

 

45+2′ ያሲን ኬኒሲ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ አስደንጋጭ ሙከራ!

 

45+1′ ከቅጣት ምት የተሞከረውን ኳስ ዘሪሁን አውጥቶታል፡፡

 

45+1′ ቢጫ ካርድ

ጋሌኒ ቻላሊ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

 

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

 

40′ ጨዋታው ወጥ የሆነ እንቅስቃሴ ሳይታይበት 40 ደቂቃዎች ደርሰዋል፡፡

 

22′ ፋርጃኒ ከሳጥኑ ጠርዝ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

 

18′ በጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴ ወደ ኤስፔራንስ የግብ ክልል ተጠግተው ምንተስኖት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሞኤዝ ቤን ቼሪፍያ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

 

17′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሮበርት ኦዶንካራ በጉዳት ወጥቶ ዘሪሁን ታደለ ተክቶት ገብቷል፡፡

 

14′ ሮበርት ኦዶንካራ ጉዳት አጋጥሞት ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡

 

2′ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አዳነ ጥሩ የግብ እድል ሊፈጥርበት የሚችለውን እድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

 

ተጀመረ!

ጨዋታው በሳላዲን ሰኢድ አማካኝነት ተጀመረ፡፡

 

09:55 ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡

_______

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

 

ሮበርት ኦዶንካራ

 

ፍሬዘር ካሳ – ሳላዲን በርጌቾ – አስቻለው ታመነ – አበባው ቡታቆ

 

ናትናኤል ዘለቀ – ምንተስኖት አዳነ

ፕሪንስ ሰርቪንሆ –  አዳነ ግርማ – አብዱልከሪም ኒኪማ

 

ሳላዲን ሰኢድ

_____________

 

09፡40 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

 

09:20 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡

 

09:05 የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ለማሟሟቅ ወደ ሜዳ እየወጡ ይገኛሉ፡፡

 

09:00 ስታድየሙ በየቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ህብረ ዜማ እና በሚውለበለቡ አርማዎች ደምቋል፡፡ ከቀኝ ወደ ግራ እየተቀባበሉ ግሩም የድጋፍ ዜማ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

 

08:45 የስታድየሙ አብዛኛው ክፍል በተመልካች እየተሞላ ይገኛል፡፡ ከውጪ ሆነው ወደ ውስጥ ለመግባት ሰልፍ የያዙ እጅግ በርካታ ተመልካቾች ይገኛሉ፡፡

 

08:30 የሁለቱም ቡድን አባላት ስታድየም ደርሰው ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *