በኢትዮጵያ የመጀመርያው መስማት የተሳናቸው የእግር ኳስ ክለብ ተመሰረተ 

በኢትዮዽያ እግር ኳስ ታሪክ የመጀመርያው መስማት የተሳናቸው የእግርኳስ ክለብ እንደሆነ የተነገረት ሰናይ መስማት የተሳናቸው የእግር ኳስ ክለብ እድሚያቸው ከሃያ አመት በታች የሆኑ ሰላሳ አምስት ታዳጊዎች በመያዝ የተቋቋመ ክለብ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሰኔ 09 /09/ 09 ላይ የእውቅና ፍቃድ የተሰጠው መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ሰናይ መስማት የተሳናቸው የእግርኳስ ክለብ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ሰራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ለታዳጊዎቹ የመጫወት እድል ለመፍጠር ከተለዩ ሀገራት ከመጡ ቡድኖች ጋር  የወዳጅነት ጨዋታዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከካናዳ ከመጣ ቡድን ጋር የተጫወተ ሲሆን ትላንት በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ከደቡብ ኮርያ ከመጣ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ተጫውቷል። የደቡብ ኮርያ አምባሳደር ፣ የኮርያ ዘማች አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበትም በድምቀት ተካሂዷል።

የዚህ ሀሳብ ጠንሳሽና የክለቡ መስራች የሆኑት የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ እንዳለኢየሱስ አባተ ክለቡ ወደ ፊት ብዙ እቅዶች እንዳሉትና ሌሎች የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገሮች መስማት በተሳናቸው ጉዳተኞች ላይ ክለቦችን በመስረት የሚያደርጉትን የሊግ ውድድር በሀገራችን በኢትዮዽያም በሁሉም ክልል ከፓራሊምፒክ በዘለለ ክለቦች ተቋቁመው ውድድሮች እንዲደረጉ እንደሚፈልጉ ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግረዋል።

ትላናት በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ የታደመችው ሶከር ኢትዮዽያ መስማት የተሳናቸው ታዳጊዎች ለመጫወት ያላቸው ጉጉት እና ፍላጎት በጨዋታው ወቅት እንደቡድንም ሆነ በግል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ስንመለከት የሰናይ ስፖርት ክለብን ፈለግ በመከተል ሌሎች የአዲስ አበባና የክልል ከተሞች ክለብ በማቋቋም ለእነዚህ ታዳጊዎች የመጫወት ዕድል በመፍጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሊያስቡበት ይገባል መልክታችን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *