መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT  መከላከያ  1-1  ወላይታ ድቻ 

21′ ሙባረክ ሽኩር (ራሱ ላይ) | 55′ አላዛር ፋሲካ(ፍቅም)

*ወላይታ ድቻ በመለያ ምቶች 4-2 አሸንፎ የ2009 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡


መለያ ምቶች
መከላከያ 2-4 ወላይታ ድቻ

5ኛ ምት
ወንድወሰን ገረመው አስቆጠረ፡፡ ድቻ አሸነፈ

4ኛ ምት
ይድነቃቸው ኪዳኔ ሳተ
አብዱልሰመድ አሊ ለድቻ አስቆጠረ

3ኛ ምት
ፈቱዲን ጀማል ሳተ
ሳሙኤል ሳሊሶ ለመከላከያ አስቆጠረ

2ኛ ምት
አላዛር ፋሲካ ለድቻ አስቆጠረ
አወል አብደላ ሳተ

1ኛ ምት
ባዬ ገዛኸኝ ለመከላከያ አስቆጠረ
ተክሉ ታፈሰ ለድቻ አስቆጠረ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተፈጸመ፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ያመራሉ፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
89′ ወንድወሰን አሸናፊ ገብቶ ወንድወሰን ገረመው ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ- ድቻ
86′ በዛብህ መለዮ ወጥቶ ያሬድ ዳዊት ገብቷል፡፡

85′ ውብሸት አለማየሁ በበኃይሉ ላይ በሰሩት ጥፋት ማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
84′ አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ ውብሸት አለማየሁ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
82′ ሚካኤል ደሰታ ወጥቶ ኡጉታ ኦዶክ ገብቷል፡፡

81′ ማራኪ ያሻገረውን ኳስ ባዬ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

80′ በዛብህ ያመቻቸለትን ኳስ አናጋው ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

77′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከሳጥኑ ጠርዝ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ለጥቂት ወጥቷል፡፡

75′ ባዬ ከሳጥን ውጪ የመታውን ኳስ ወንድወሰን መልሶታል፡፡

74′ ቴዎድሮስ ታፈሰ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል አቅራቢያ የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ጨርፎ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ!
68′ አብዱልሰመድ አሊ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

66′ ፈቱዲን ጀማል ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አላዛር ስቶታል፡፡ ግብ ለመሆን እጅግ የቀረበ ሙከራ ነበር፡፡ ድቻ በሁሉም ረገድ ጨዋታውን ተቆጣጥረውታል፡፡

የተጫዋቾ ለውጥ – መከላከያ
64′
ሳሙኤል ታዬ ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

63′ አላዛር ፋሲካ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወጥቷል፡፡ ድቻ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
61′
መስፍን ኪዳኔ ወጥቶ ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቷል፡፡

ጎልልል! ድቻ
55′ አላዛር ፋሲካ የፍጹም ቅጣት ምተቱን በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮ ድቻን አቻ አድርጓል፡፡

ፍቅም!
53′
ይድነቃቸው ኪዳኔ በአናጋው ላይ በሰራው ጥፋት የፍጹም ቅጣት ምት ለድቻ ተሰጥቷል፡፡ ለይድነቃቸው የማስጠንቀቂያ ካርድ ተሰጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ!
49
‘ ባዬ ገዛኸኝ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

44′ ድቻዎች በመከላከያ የግብ ክልል ተቀባብለው አላዛር የሞከረውን ኳስ ይድነቃቸው በግሩም ሁኔታ አድኖታል፡፡

40′ ከመሀል ሜዳ ቅብብል እና ተደጋጋሚ ጥፋቶች ውጪ ጨዋታው የሚጠቀስ እንቅስቃሴ እየታየበት አይገኝም፡፡

30′ ድቻ የተሻለ መንቀሳቀስ ቢችልም ጨዋታው እየተቀዛቀዘ ይገኛል፡፡ ሜዳው (በተለይ መሀለኛው የሜዳ ክፍል) ኳስ ለማንሸራሸር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

ጎልልል! መከላከያ!
21′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ ሙባረክ ለማውጣት ሲሞክር በራሱ ጎል ላይ አስቆጥሯል፡፡

15′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ሁለቱም ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት ቢያደርጉም በማጥቃት ወረዳው ላይ ሲደርሱ እየተቋረጠ ይገኛል፡፡

13′ አማኑኤል ያሻማውን የማዕዘን ምት አናጋው በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

5′ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በሚስማር ተራ ተሰብስበው ቡድናቸውን እየያበረታቱ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በወላይታ ድቻ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


10:15 ቡድኖቹ ሜዳ ገብተው ከክብር እንግዶች ጋረር ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡

ዳኞች

ዋና ዳኛ – በአምላክ ተሰማ

ረዳቶች – ፋሲካ የኀላሸት እና ካሳሁን ፍፁም 

4ኛ ዳኛ – ጎኔ ንዳ

ኮሚሽነር – ተስፋዬ ኦሜጋ

የመከላከያ አሰላለፍ


22 ይድነቃቸው ኪዳኔ


2 ሽመልስ ተገኝ – 12 ምንተስኖት ከበደ – 4 አወል አብደላ – 5 ታፈሰ ሰርካ


19 ሳሙኤል ታዬ – 21 በኃይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ


9 ሳሙኤል ሳሊሶ – 17 ባዬ ገዛኸኝ – 10 መስፍን ኪዳኔ

ተጠባባቂዎች
1 አቤል ማሞ
28 ሚልዮን በየነ
29 ሙሉቀን ደሳለኝ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
26 ኡጉታ ኦድክ
7 ማራኪ ወርቁ
11 ካርሎስ ዳምጠው


የወላይታ ድቻ አሰላለፍ


1 ወንድወሰን አሸናፊ


6 ተክሉ ታፈሰ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 3 ቶማስ ስምረቱ – 7 አናጋው ባደግ

8 አማኑኤል ተሾመ – 20 አብዱልሰመድ አሊ

17 በዛብህ መለዮ – 4 ዮሴፍ ድንገቱ – 2 ፈቱዲን ጀማል

19 አላዛር ፋሲካ

ተጠባባቂዎች
12 ወንድወሰን ገረመው
21 ውብሸት አለማየሁ
23 ጸጋዬ ብርሀኑ
25 ዘላለም እያሱ
16 ፍራኦል መንግስቱ
11 ፉአድ ተማም
9 ያሬድ ዳዊት


09:58 ቡድኖቹ አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

09:30 ሁለቱም ቡድኖች ለማሟሟቅ ሜዳ ገብተዋል፡፡

እንዴት ደረሱ?

መከላከያ በሁለተኛው ዙር ሀዋሳ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ሲያልፍ የአምናው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመለያ ምቶች አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ችሏል፡፡ በመቀጠልም ወልድያን አሸንፎ ለፍጻሜው ደርሷል፡፡

ወላይታ ድቻ በሁለተኛው ዙር አርባምንጭ ከተማን 1-0 ፣ በሩብ ፍጻሜው ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመለያ ምቶች እንዲሁም በግማሽ ፍጻሜው ጅማ አባ ቡናን 1-0 በማሸነፍ ለፍጻሜው ቀርቧል፡፡

የጥሎ ማለፍ ሪከርድ

መከላከያ ውድድሩን ለ13 ጊዜያት በማሸነፍ ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡ ወላይታ ድቻ ደግሞ ለፍጻሜው ሲቀርብ ይህ የመጀመርያው ነው፡፡

የቅርብ ግንኙነት

ሁለቱ ክለቦች ዘንድሮ ሁለት ጊዜ በሊጉ ተገናኝተው የመጀመርያውን ድቻ 2-0 ሲያሸንፍ ሁለተኛውን ያለግብ በአቻ ውጤት ፈፅመዋል፡፡


ሰላም ክቡራት እና ክቡራን!

የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ በዛሬው እለት 10:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም በመከላከያ እና ወላይታ ድቻ መካከል ይደረጋል፡፡ በዚህ ገፅ ላይም ጨዋታውን በቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡ ይህነን ገፅ Refresh/Reload በማድረግ የጨዋታውን ዋና ዋና እንቅስቃሴ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *