ማርያኖ ባሬቶ 38 ተጫዋቾችን አሳወቁ

 

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቅርቡ ዝግጅት የሚጀምረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ 38 ተጫዋቾችን መርጧል፡፡

ባለፉት 2 የውድድር ዘመናት ከብሄራዊ ቡድን ጋር አብረው የነበሩ ፣ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች እና ለመጀመርያ ጊዜ የተመረጡ ተጫዋቾች በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በዝርዝሩ የሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን ከ20 አመት በታች ቡድኑ 3 ተጫዋቾችን አስመርጧል፡፡ ክለብ አልባ የሆነው ፍቅሩ ተፈራ እና ዘንድሮ አመዛኙን የውድድር ዘመን በተጠባባቂነት ያሳለፈው ሲሳይ ባንጫ መካተታቸው እንዲሁም በሊጉ ድንቅ አቋማቸውን ያሳዩት ፍሬው ሰለሞን ፣ ባዬ ገዛኸኝ እና ኤልያስ ማሞን የመሳሰሉ ተጫዋቾች አለመካተታቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡

የ38 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል ፡-

ግብ ጠባቂዎች (4)

ጀማል ጣሰው (ቡና) ፣ ታሪኩ ጌትነት (ደደቢት) ፣ አሰግድ አክሊሉ (ሙገር) ፣ ሲሳይ ባንጫ (ደደቢት)

ተከላካዮች (12)

አሉላ ግርማ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አበባው ቡታቆ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ብርሃኑ ቦጋለ ፣ አክሊሉ አየነው ፣ ስዩም ተስፋዬ (ደደቢት) ፣ ቶክ ጄምስ ፣ ሮቤል ግርማ (ቡና) ፣ ማታይ ሉል (ናሽናል ሲሚንቶ) ፣ ሽመልስ ተገኝ (መከላከያ) ፣ ግርማ በቀለ (ሀዋሳ ከነማ)

አማካዮች (16)

ምንያህል ተሸመ ፣ አዳነ ግርማ ፣ አንዳርጋቸው ረታ ፣ በኃይሉ አሰፋ ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ አስቻለው ግርማ ፣ ኤፍሬም አሻሞ ፣ መስኡድ መሃመድ (ቡና) ፣ ታደለ መንገሻ ፣ ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት )፣ ሽመልስ በቀለ (ክለብ የለውም) ፣ አስራት መገርሳ (ዳሽን) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከነማ) ፣ አዲስ ህንፃ (አህሊ ሼንዲ)

አጥቂዎች (6)

ኡመድ ኡኩሪ ፣ ፍጹም ገብረማርያም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዳዊት ፍቃዱ (ደደቢት) ፣ ሳላዲን ሰኢድ (ዋዲ ዴግላ) ፣ ጌታነህ ከበደ (ቢድቬትስ ዊትስ) ፣ ፍቅሩ ተፈራ (ክለብ የለውም)

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *