ብሄራዊ ሊግ ወደ መጠናቀቂያው እየተቃረበ ነው

ብሄራዊ ሊግ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው ፤ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ቡድኖችም እየታወቁ ነው፡፡ የ2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ በ7 ዞኖች ተከፍሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሊጉ ወደ መጠናቁ በደረሰበት ወሳኝ ሰዓት ከየዞኖቹ ወደ ቀጣዩ እና መጨረሻው ዙር ያለፉ ቡድኖች አብዛኞቹ ታውቀዋል፡፡

አሰልቺ እና አድካሚ የሆነው ብሄራዊ ሊግ ከኢትዮጵያ ፕሪምየሪ ሊግ ቀጥሎ የሚገኝ ሊግ ነው፡፡ የዳኝነት፣ የስርዓት አልበኝነት እና ከአቅም በታች መጫወት ችግሮች የሚታዩበት ሊጉ ከሞላ ጎደል ወደ መጠናቀቁ ደረጃ ደርሷል፡፡16 ቡድኖችም ከ7ቱ ዞን ከሚገኙት ቡድኖች እየታወቁ ይገኛሉ፡፡

ከየምድቡ 1ኛ እና 2ተኛ የወጡ ቡድኖች በቀጥታ ሲያልፉ 2 ጥሩ 3ተኛ የሆኑ ቡድኖችም ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ፡፡ ማዕከላዊ ዞን በሁለት ምድቦች የተከፈለ ሲሆን፡፡ ምድብ ሀ ላይ ሱሉልታ ከነማ እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ከዚሁ ምደብ የኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች እና ሰበታ ከነማ ጥሩ 3ተኛ ሆኖ ለማለፍ እየተፎከሩ ይገኛል፡፡ ውሀ ስራዎች 32 ነጥብ አለው ሰበታ ደግሞ 33 ነጥብ ላይ ይገኛል፡፡ ውሀ ስራዎች ሁለት ቀሪ ጨዋታዎቹን ከንፋስ ስልክ እና ሀይኮፍ ጋር ያደርጋል፡፡ ውሀ ስራዎች ሀይኮፍን 10ለ1 ቢያሸንፍም ሰበታ ከነማ ባቀረበው ቅሬታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የጨዋታውን ውጤት ሰርዞ እንደገና እንዲደገም መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡ ሀይኮፍ ከአቅም በታች በመጫወቱ ነበር ውጤቱ የተሰረዘው፡፡ ሀይኮፍ ባሳለፍነው ሳምንትም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 9ለ0 መሸነፉ ብዙዋችን አስገርሟል፡፡

በምድብ ለ አንድም ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ገና አላረጋገጠም፡፡ አዲስ አበባ ፓሊስ በ37 ነጥብ እና ልደታው ኒያላ በ36 ነጥብ ምድቡን ይመራሉ፡፡ ደብረ ብርሃን እና ቡራዩ ከነማ በ34 እና በ33 ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

በምዕራብ ዞን ሆሳና እና በቀድሞ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ (ድሬ) የሚሰለጥነው ወልቂጤ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ወልቂጤ ከነማ ከሜዳው ውጪ ከፋ ቡናን 1ለ0 በማሸነፉ ነው በ37 ነጥብ ወደ ተከታዩ ዙር ያለፈው፡፡ አለም ገበያ ጥሩ 3ተኛ ለመሆን በ33 ነጥብ እየተፎካከረ ይገኛል፡፡

በምስራቅ ዞን በ2005 በአስገራሚ መልኩ ከፕሪምየሪ ሊጉ የወረደው አዳማ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ በበረከት አዲሱ ጎሎች በቀላሉ ተጋጣሚዋቹን እያሸነፈ ነው አዳማ ከነማ 16ቶቹን የተቀላቀለው፡፡ ድሬዳዋ ከነማ እና ወንጂ በ31 እና በ30 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ እየተፎካከሩ ይገኛሉ፡፡

በደቡብ ዞን ሻሸመኔ ከነማ 16ቶቹን ተቀላቅሏል፡፡ ጂንካ እና በክፍሌ ቦልተና የሚሰለጥነው ደቡብ ፓሊስ በእኩል 33 ነጥብ ሻሸመኔን ተከትሎ ለማለፍ ተፋጠዋል፡፡ አላባ ደግሞ ለተሻለ 3ተኛነት ይፎካከራል፡፡

ሰሜን ዞን ልክ እንደ ማዕከላዊ ዞን በምድብ ሀ እና ለ ተከፍሎ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛል፡፡ በምድብ ሀ ባህር ዳር ከነማ እና ፋሲል ከነማ በ29 እና በ26 ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡


በምድብ ለ ወልዲያ በ30 እንዲሁም ጥቁር አባይ በ29 ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ 16 ቡድኖች ሚሳተፉበትን የመጨረሻ የብሄራዊ ሊግ ዙር ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለማለፍ ሙከራ ያደረገው መቀሌ ከነማ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

16 ቡድኖች የሚካፈሉበት የመጨረሻ ዙር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ጨዋታዎች ከሰኔ 25 ጀምሮ ይካሄዳሉ፡፡ ውድድሩ የት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የጠራ መረጃ ያልሰጠ ሲሆን ባህር ዳር ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *