ክለቦች ለ2010 የውድድር ዘመን ራሳቸውን ለማጠናከር የተለያዩ ተጨዋቾችን እያስፈረሙ እንዲሁም የአሰልጣኝ ቅጥሮችን እያከናወኑ ይገኛሉ። በከፍተኛው ሊግ የሚወዳደረው ሰበታ ከተማም አሰልጣኝ ስዩም ከበደን የቡድኑ ዋና አሰልጠኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
አዲስ አበባ ከተማን ከከፍተኛው ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያሳደጉትና እስከ ውድድር አመቱ አጋማሽ በክለቡ የቆዩት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከክለቡ ጋር ከተለያዩ በኋላ ያለፉትን 6 ወራት ያለ ስራ ቆይተው በከፍተኛ ሊጉ የሚወዳደረው ሰበታ ከተማን በ1 አመት ውል ተቀላቅለዋል፡፡ ክለቡንም በ2003 ወደወረደበት ፕሪምየር ሊግ የመመለስ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡
አሰልጣኝ ስዩም ከዚህ ቀደም አዳማ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አልሳቅር ፣ አልዋሂዳ ሰንአ ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድንን በረዳት አሰልጣኝነት ያሰለጠነ ማሰልጠን ችለዋል፡፡