አዲሱ የፕሪምየር ሊግ መቐለ ከተማ የሊጉ ውድድር ገና ሳይጀመር ከዋና አሰልጣኙ ጌታቸው ዳዊት መለያየቱ ተረጋግጧል፡፡
አሰልጣኙ በ2008 የውድድር ዘመን አጋማሽ ከደደቢት ከተሰናበቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለባቸው መቐለ ከተማ ተመልሰው ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ የቻሉት አሰልጣኝ ዳዊትን ያሰናበተበትን ምክንያት ለመስቀል በአል ከወልዋሎ ጋር ሊካሄድ የነበረውን ጨዋታ ካለ ክለቡ ፍቃድ እንዳይካሄድ ማድረጋቸውና ሌሎች ምክንያቶች በሁለቱ መካከል ክፍተቶች ፈጥሮ ለመለያየት እንዳበቃቸው ተነግሯል፡፡
ክለቡ በአሰልጣኝ ጌታቸው ምትክ ማንን ቀጣዩ አሰልጣኝ እንደሚያደርግ ያልተገለጸ ሲሆን የአሰልጣኙ ረዳት የነበሩት ጎይቶም ኃይለ በጊዜያዊነት ቡድኑን መረከባቸው ታውቋል፡፡ ፕሪምየር ሊጉ ሊጀመር በተቃረበበት ሰአት አሰልጣኙን ማሰናበቱ ባለመረጋጋት ውስጥ ሆኖ አዲሱን የውድድር ዘመን የመጀመር ስጋት ውስጥ ገብቷል፡፡