የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተፈፅሟል፡፡ የፈረሰኞቹ አጥቂ ኡመድ ኡኩሪም በ16 ግቦች የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ክብር ተቀዳጅቷል፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለግብፁ ኢትሃድ አሌሳንድሪያ ለመጫወት የተስማማው ኡመድ የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብር ሲወስድ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡
ከ1990 ጀምሮ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎቹ የሚከተሉት ናቸው
1990.ሀሰን በሽር(መድን)-9
1991.በረከት ሀጎስ(ሀዋሳ ከነማ)-8
1992.ስንታየሁ ጌታቸው(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-12
1993.ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል)-24
1994. ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል)-20
1995. ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል/ኢትዮጵያ ቡና)-14
አህመድ ጁንዲ(ምድር ባቡር)-14
1996.መሳይ ተፈሪ(አርባምንጭ ጨጨ)-13
ታፈሰ ተስፋዬ – 13
1997.መዳህኔ ታደሰ(ትራንስ ኢ.)-18
1998.ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)-21
1999. ታፈሰ ተስፋዬ (ኢትዮጵ ቡና) 11 (10 ክለቦች አቋርጠው እስኪወጡ ድረስ)
2000.ሳላዲን ሰኢድ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-21
2001.ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)-23
2002. ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)21
2003.አዳነ ግርማ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-20
ጌታነህ ከበደ(ደደቢት)-20
2004.አዳነ ግርማ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-23
2005.ጌታነህ ከበደ (ደደቢት) – 22
2006.ኡመድ ኡኩሪ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) – 16
(C) Soccer Ethiopia