ኢትዮጵያ ቡና ከታደለ መንገሻ ጋር እየተደራደረ ይገኛል

ኢትዮጵያ ቡና የመስመር አማካይ ተጫዋች ከሆነው ታደለ መንገሻ ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑን ከክለቡ ማወቅ ችለናል፡፡ ከደደቢት ጋር ውሉን የጨረሰው ታደለ ወደ ቡና መዛወር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም ተነግሯል፡፡
ከደደቢት ክለብ በኩል ባገኘነው መረጃ ክለቡ ታደለ ወደ ውጪ ሃገር ብቻ እንደሚሄድ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ ታደለ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን የብቃት መውረድ የታየበት ሲሆን በ2006 ከነበረው አቋም የወረደ አቋም አሳይቷል፡፡ ታደለ ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት መፈለጉ ነገሮችን ለቡና ሊያቀሉት ይችላሉ፡፡ ድርድሩም በመልካም ሁኔታ እየሄደ ሲሆን ታደለ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ቡና ፈራሚ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ መድህን እና ደደቢት የተጫወተው ታደለ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወት ችሏል፡፡ ታደለ ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የ2014 የቻን ዋንጫ በዋሊያዎቹ ቡድን ውስጥ ነበር፡፡
በዝውውር ገበያው ላይ የተቀዛቀዘው ኢትዮጵያ ቡና እስካሁን አብዱልከሪም መሃመድን አስፈርሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *