ታረቀኝ አሰፋ ‹‹ ዳኜ ›› የዳሽን ቢራ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ በተጓዥነታቸው ቀጥለዋል፡፡ በ3 አመታት ውስጥ 5ኛ ቡድናቸውንም ተረክበዋል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከነማ እና ኒያላ ተጫዋች በውድድር ዘመኑ አጋማሽ አሰልጣኝ ዘሪሁን በፍቃዱን ተክተው የሀዋሳ አሰልጣኝ ሆነው ቢሾሙም 6 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ክለቡን መልቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

ዳሽን ቢራ የአሰልጣኙ ማረፊያ ሲሆን የውድድር ዘመኑን አመዛኝ ጊዜ ዳሽንን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ካሊድ መሃመድ የ ‹‹ ዳኜ ››ምክትል ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

አሰልጠያኝ ታረቀኝ አሰፋ በቅርብ አመታት መረጋጋት አልታየባቸውም፡፡ በ2002 ሲዳማ ቡናን ወደ ፕሪሚየር ሊጉን ካሳደሩ በኋላ 2 የውድድር ዘመናትን በክለቡ ቆይተው ወደ ሰበታ ከነማ አቅንተዋል፡፡ 2005 ደግሞ የኢትዮጰያ ብሄራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኙ ስዩም ከበደን አሰናብቶ የሰውነት ቢሻው ምክትል አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡ በ2006 መጀመርያ ከሰውነት ቢሻው ጋር አብረው የተሰናበቱት አሰልጣኝ ታረቀኝ ለግማሽ የውድድር ዘመን ሀዋሳ ከነማን መርተው ለከርሞ ዳሽን ቢራን ለማሰልጠን ተስማምተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *