የብሄራዊ ሊጉ የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ነገ የሚደረጉት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት እንደሚካሄዱ ቢገልፅም ከአንድ ሰአት በፊት ደግሞ አላፊውን የሚለዩት 2 ጨዋታዎች ብቻ በተመሳሳይ ስታድየም እንደሚደረጉ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
03፡00 – ድሬዳዋ ከነማ ከ ፋሲል ከነማ – ድሬዳዋ ስታድየም
03፡00 – ፌዴራል ፖሊስ ከ አርሲ ነገሌ – ሳቢያን ሜዳ
05፡00 – ወልዋሎ ከ ቡራዩ – ድሬዳዋ ስታድየም
-የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴው በወሰነው ውሳኔ መሰረት ነገ የማለፍ እድል ያላቸው ክለቦች በተመሳሳይ ሰአት ሲጫወቱ አስቀድመው ከውድድሩ መሰናበታቸውን ያረጋገጡት ወልዋሎ እና ቡራዩ ከነማ በ5፡00 በድሬዳዋ ስታየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የሌሎቹ ምድቦች ጨዋዎች ግን በሶስቱ ሜዳዎች በተመሳሳይ ሰአት ይደረጋሉ፡፡
-ሳቢያን/መከላከያ ሜዳ የሚደረገው ጨዋታ ከተቋረጠ በድሬዳዋ ስታድየም የሚደረገውም ጨዋታ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
-ጨዋታዎቹ ጠዋት እዲሆኑ የተወሰነው ምናልባት ጨዋታው ቢቋረጥ/ባይደረግ ሁኔታዎችን አመቻችተው ከሰአት ለማጫወት እንዲመች እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
-በተመሳሳይ ሰአት የሚደረጉት ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ሜዳዎች የተለዩት በእጣ ነው፡፡
-የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴው እንዳስታወቀው ሌሊቱን በሳቢያን ሜዳ ዝናብ የሚዘንብ ከሆነ ጨዋታው በመከላከያ ሜዳ ይደረጋል፡፡
-የየምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች በየቀኑ ተደርገው ሰኞ ወደ ሩብ ፍፃሜ የሚያልፉት ቡድኖች ሙሉ ለሙሉ ይታወቃሉ፡፡ በዚህም መሰረት ቅዳሜ የምድብ 2 ፣ እሁ8ድ የምድብ 3 እንዲሁም ሰኞ የምድብ አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡
-ውድድሩ ለ2 ቀናት እረፍት ያደርግና የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከሀሙስ ጀምሮ ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡