ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታድየም በተደረገው ጨዋታ መገባደጃ ደቂቃዎች ላይ ለተፈጠረው ሁከት ተጠያቂ የተደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 1 ጨዋታ በዝግ ስታዲየም እንዲጫወት እና የ180ሺህ ብር ቅጣት መጣሉ የሚታወስ ነው።
ከውሳኔው በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅጣቱ አግባብ አይደለም በሚል ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ የቅጣት ውሳኔው በይደር ቆይቶ ሲታይ የሰነበተ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም አንድ ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲካሄድ የተወሰነውን ውሳኔ በመሻር በተመልካች ፊት እንዲካሄድ ፣ የገንዘብ ቅጣቱንም ወደ 140ሺህ እንዲቀንስ ወስኗል።
በውሳኔው መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነገው እለት በሜዳው ፋሲል ከተማን የሚያስተናግድበት ጨዋታ በተመልካች ፊት የሚደረግ ይሆናል።