ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንታዊ እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ግንቦት 26 ሊደረግ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለምርጫው ብቁ ናቸው ያላቸውን ተወዳዳሪዎች ያሳለፈ ሲሆን በምርጫው የመወዳደር እድል ያላገኙ ተወዳዳሪዎች ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታቸውን አቅርበው ነበር፡፡
ቅሬታዎችን ሲመለከት የቆየው ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ዛሬ የመጨረሻ ውሳኔውን አሳውቋል፡፡ በምርጫ አስፈፃሚው የመወዳደር እድል የተሰጣቸው ግለሰቦች አሁንም በምርጫው ላይ የተገኙ ሲሆን አቶ ተስፋይ ካህሳይ በምርጫው ላይ ለፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቦርድ አባል አቶ ተስፋይ ከትግራይ ክልል እግርኳስ ፌድሬሽን ድጋፍ አግኝተው የነበረ ቢሆንም የክልሉ ፌድሬሽን ባሳለፍነው ሰኞ ድጋፉን ማንሳቱን አሳውቆ ነበር፡፡ ሆኖም የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውሳኔው ሽሮ አቶ ተስፋይ በምርጫው ላይ እንዲሳተፉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የክልል እግርኳስ ፌድሬሽን ድጋፉን ያነሳው የተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር ለአስመራጭ ኮሚቴው ከተላለፈ በኃላ እና ለውሳኔውም በቂ ምክንያት አለማቅረቡም ጥያቄዎች ሲያስነሳበት ቆይቷል፡፡
ለፕሬዝደንትነት ለመወዳደር ድጋፍ አግኝተው የነበሩት ኢንጅነር ፀደቀ ይሁኔ እና ኢንጅነር ቾል ቤል በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴውም ያቀረቡት ቅሬታ ውድቅ ተደርጓል፡፡
የአቶ ተስፋይ ወደ ውድድር መመለስን ተከትሎ በአጠቃላይ አራት ግለሰቦች በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ይሳተፋሉ፡፡ 22 ግለሰቦች ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ለመመረጥ ግንቦት 26 በሚደረገው ምርጫ ይፎካከራሉ፡፡ ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ሆነው በምርጫው ላይ ቀርበዋል፡፡
ሙሉ የእጩዎች ዝርዝር