ኢትዮጵያ ቡና 2-1 ድሬዳዋ ከተማ | የአሰልጣኞች አስተያየት

አዲስ አበባ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሳምሶን ጥላሁን እና አቡበከር ነስሩ ግቦች ታግዞ ድሬዳዋ ከተማን 2ለ1 መርታት ችሏል፡፡ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

” በ90 ደቂቃው በወጥነት መጫወታችን ለድል አብቅቶናል” አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለጨዋታው…

“የዛሬው ጨዋታ ጥሩ ነበር ፤ ተጋጣሚያችን ላይ ብልጫ ወስደን መጫወት ችለናል። ነገርግን በቀጣይ የመልሶ ማጥቃት ተጋላጭ እንዳንሆን ይበልጥ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ጠንካራ የመከላከል አደረጃጀት ነበረን ፤ በ90 ደቂቃው በወጥነት መጫወታችንም ለድል አብቅቶናል፡፡”

ስለአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ እና ቡድናቸው…

“ለአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የተለየ ክብር አለኝ፡፡ እሱ የተለየ አሰልጣኝ ነው ፤ የተለየ የአጨዋወት መንገድ አለው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን እሱ ከሚሰራቸው ቡድኖች ጋር ተጫውቶ ማሸነፍ ከባድ ነው። ነገርግን ይህን ቡድን ማሸነፍ በመቻላችን ደስተኛ ነኝ፡፡”


” በዚህ ሁሉ ደጋፊ ታጅቦ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታን ማድረግ ቀላል አይደለም” አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ – ድሬዳዋ ከተማ

ስለጨዋታው…

“ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ደጋፊ ታጅቦ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታን ማድረግ ቀላል አይደለም ነገርግን አቅማችን የፈቀደው ያህል ተቋቋመን ለመጫወት ጥረት አድርገናል፡፡”

“የተገኙ አጋጣሚዎች ቢኖሩም በፊት መስመር ተሳላፊዎቻችን ለውሳኔ መቸኮል አላሳካናቸውም። እንዲሁም የቆሙ ኳሶች አጠቃቀም ላይ ክፍተቶች ነበሩብን። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ደጋፊ ፊት የመጀመሪያ ጨዋታዎችንን እንደማድረጋችን ከደጋፊው ተጽዕኖ ጋር ተዳምሮ ውጤት አልቀናንም ፤ በቀጣይ አሻሽለን እንቀርባለን፡፡”


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ