ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፖርቱጋላዊ ወደ እንግሊዛዊ ?

ከ1996 ጅምሮ ለሀገር ውስጥ አሰልጣኞች ጀርባውን የሰጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ የውጪ ሀገር አሰልጣኝ ሊቀጥር ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ቫስ ፒንቶ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት ቢቀረውም ከውጤት መጥፈት ጋር ተያይዞ ባሳለፍነው ቅዳሜ መለያያቱ ይታወቃል። ክለቡ በቀጣይ በሊጉ ጅማሮ የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ ይቀጥራል ወይስ ሌላ የውጭ አሰልጣኝ መቅጠሩን ይቀጥላል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

በአሁኑ ወቅት ክለቡ ከሀገር ውስጥ አሰልጣኞች ፊቱን እንዳዞረ እንደሚቀጥል የሚያሰዩ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን የሰርቢያ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞችን አነጋግሮ እንደጨረሰ እና ዛሬ የክለቡ የቦርድ አመራር በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ የወደፊቱ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማን እንደሆነ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። እንዳገኘናቸው መረጃዎች ከሆነም እንግሊዛዊው አሰልጣኝ የተሻለ ዕድል ያላቸው ይመስላል።

ዓምና የ2010 ውድድር መግቢያ ላይ ከሆላንዳዊ አሰልጣኝ ማርቲ ኑይ ጋር ተለያይቶ ፖርችጋላዊው አሰልጣኝ ቫስ ፒንቶን የቀጠረው ክለቡ በተመሳሳይ መልኩ የ2011 የውድድር መግቢያ ላይ ቫስ ፒንቶን አሰናብቶ ሌላ የውጭ አሰልጣኝ የሚቀጥር መሆኑ አስገራሚ ሆኗል። የአሰልጣኝ ቅጥሩ ከተፈፀመ ከ1996 ጀምሮ በአስር የውጪ አሰልጣኞች ስር ያለፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ1998ቱ የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ኬን ሞርተን በኋላ በመጀመሪያው ብሪታንያዊ አሰልጣኝ የሚመራ ይሆናል።


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ