መስማት የተሳናቸው የእግር ኳስ ፌስቲቫል ነገ ይጀምራል

ስድስት የክልል ቡድኖች የሚሳተፉበት መስማት የተሳናቸው የእግር ኳስ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

ድሬዳዋ ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ ፣ ሀዋሳ ፣ ሆሳዕና እና አዲስ አበባ የመጡ ቡድኖች እንዲሁም ቁጥራቸው ከ200 በላይ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት የመጀመርያ የሆነ መስማት የተሳናቸው የእግርኳስ ፌስቲቫል ከጥቅምት 20 – 25 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚደረግ ይጠበቃል። 

በኤፎ አድቨርታይዚንግ አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል እግርኳስን የሚሰሙ ብቻ ሳይሆን መስማት የተሳናቸውም መጫወት እንደሚችሉ የተቀረው ዓለም እንደሚያደርገው ኢትዮጵያም ማሳየት እንዳለባት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ፌስቲቫል ነው። 

ውድድሩ ነገ ከጠዋቱ 03:30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በሚደረገው የመክፈቻ ጨዋታ  በድምቀት የሚጀምር ይሆናል።