የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ዲላ ከተማ ትኩረቱን ወጣቶች ላይ በማድረግ የአራት ተጫዋቾችን በቋሚ ፊርማ እና በውሰት ውል ሲቀላቅል ሁለት ረዳት አሰልጣኞችኝም ቀጥሯል ፡፡
ክለቡ በክረምቱ ለበርካታ ተጫዋቾች የሙከራ ዕድልን የሰጠ ሲሆን በርካታ ውል የሚቀራቸው ተጫዋቾች በክለቡ ውስጥ ስላሉ ጥቂት ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የሚቀላቅል ይሆናል። በዚህም መሰረት ዳግም ተፈራ (ከሀዋሳ ከተማ/ግብ ጠባቂ) ኢብራሂም ቢያኖ (ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከ20 አመት በታች/አጥቂ)፣ ኤፍሬም (ከቅዱስ ጊዮርጊስ) እንዲሁም የቀድሞውን የክለቡን ተጫዋች ፍፁም ከበደን (ከሀምበሪቾ/አጥቂ) ያስፈረመ ሲሆን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ያደገው ዮሀንስ ዘገዬን በውሰት ለማስፈረም ማቀዱን አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመራው ዲላ ከተማ ሁለት ረዳት አሰልጣኞችን ቀጥሯል። ምክትል አሰልጣኙን ምንተስኖት መላኩን ለሀዲያ ሆሳዕና አሳልፎ የሰጠው ክለቡ ውብሸት ደስታ እና ስመኘው ገመዴ የተባሉ ሁለት አሰልጣኞችን በረዳት እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ሾሟል።
ክለቡ የ2011 ዝግጅቱን ከጀመረ አንድ ሳምነት አስቆጥሯል፡፡