የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን በየአመቱ የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) በመጪው እሁድ ይጀመራል፡፡
ካስትል ቢራ ስፖንሰር ያደረገው ይህ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ የተደረገ ሲሆን 6 የመዲናዋ ክለቦች እና 2 ተጋባዥ ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለዋል፡፡
የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል…
ምድብ አንድ ፡- ኢትዮጵያ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አዳማ ከነማ እና ደደቢት
ምድብ ሁለት ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ መከላከያ እና መብራት ኃይል
ውድድሩ እሁድ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአዲስ አበባ ስታድየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይከፈታል፡፡