ቅዱስ ጊዮርጊስ የ3 ተጫዋቾቹን ኮንትራት ማራዘም ይፋ አደረገ

የ2006 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት ማራዘሙን በክለቡ ልሳን ጋዜጣ አስታውቋል፡፡

ለፈረሰኞቹ ፊርማቸውን ያኖሩት ቢድግልኝ ኤልያስ ፣ አዳነ ግርማ እና አሉላ ግርማ ሲሆኑ እያንዳዳቸው የ2 አመት ኮንትራት ፈርመዋል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ያደገው አሉላ ግርማ ስሙ ከዳሽን ቢራ እና የውጪ ሃገራት ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየ ሲሆን ለኮንትራት ማራዘምያው እስከ 1 ሚልዮን ብር እንደተከፈለው ተነግሯል፡፡ አሉላ ከስምምነቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት ‹‹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንደምለቅ ሲወራ ቢቆይም አሁንም ልቤ እዚሁ ነው፡፡ በቢጫው ማልያ ለበርካታ አመታት መቆየት እፈልጋለሁ፡፡ ›› ብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጶያ ብሄራዊ ቡድን እና የናሽናል ሲሚንቶው አጥቂ ዳዋ ኢቲሳ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገውን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የቡድኑ ወሳኝ የመሃል ተከላካይ አይሳክ ኢሴንዴ ወደ መብራት ኃይል መዘዋወሩ ተነግሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *