ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ባህር ዳር ከተማ ከ ደደቢት

ከነገ ወደ ዛሬ እንዲመጣ የተደረገው የባህር ዳር እና ደደቢት ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል።

ከሳምንቱ የወልዋሎ እና ፋሲል ጨዋታ በመቀጠል ዛሬ በባህር ዳር ስታድየም 09፡00 ላይ የሚከናወነው ይህ ጨዋታ በአማራ እና ትግራይ ክለቦች መካከል የሚደረግ ሁለተኛው ጨዋታ ይሆናል። በዘጠነኛው ሳምንት ድሬዳዋ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈት የገጠማቸው ባለሜዳዎቹ ባህር ዳሮች ከዚያ አስቀድሞም በሜዳቸው ከመከላከያ ጋር ነጥብ መጋራታቸው ይታወሳል። በመሆኑም በነገው ጨዋታ ወደ መልካም አጀማመራቸው ለመመለስ የሚጫወቱ ይሆናል። ከተጋጣሚው በተቃራኒ ሳምንት የመጀመሪያ የሊግ ድሉን ያገኘው ደደቢትም ከወራጅ ቀጠናው በቶሎ ለመውጣት ካስፈለገው ከባህር ዳር ውጤት ይዞ መመለስ ይኖርበታል። ቡድኑ ከአምስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወላይታ ድቻን ባሸነፈበት ጨዋታ ያስቆጠራት የየዓብስራ ተስፋዬ ጎልም እንዲሁ የመጀመሪያው ጎሉ ሆና የተመመገበች ነበረች። 

በጨዋታው ሁለቱም ቡድኖች ጉዳት ላይ ይገኙ የነበሩ ተጫዋቾቻቸው የተመለሱላቸው ሲሆን በቅጣትም የሚያጡት ተጫዋች አይኖርም። 

የእርስ በርስ ግንኙነቶች እና እውነታዎች

– ሁለቱ ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ የመጀመሪያ የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ያደርጋሉ።
                          

– ባህር ዳር ከተማ በሜዳው ካደረጋቸው ሦስት የሊግ ጨዋታዎች መካከል በሁለቱ ነጥብ ሲጋራ አንዱን በድል አጠናቋል።

– ከመቐለ ውጪ ሁለት ጨዋታዎችን ያደረገው ደደቢት ሦስት ግቦች ተቆጥረውበት ያለምንም ነጥብ ተመልሷል።

ዳኛ

– ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት ይመራዋል። አርቢትሩ በሦስት ጨዋታዎች አስራ አምስት የቢጫ እና አንድ የቀይ ካርዶችን መዟል። የቀይ ካርዱ በሸገር ደርቢ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ፓትሪክ ማታሲን ከሜዳ ያስወገደ ነበር።

ግምታዊ አሰላለፍ

ባህርዳር ከተማ (4-3-3)

ምንተስኖት አሎ

ሣለአምላክ ተገኝ – ወንድሜነህ ደረጄ  – አቤል ውዱ – አስናቀ ሞገስ

ዳንኤል ኃይሉ  –  ፍቅረሚካኤል ዓለሙ – ኤልያስ አህመድ

ፍቃዱ ወርቁ – ጃኮ አራፋት – ግርማ ዲሳሳ  

                                                             
ደደቢት (4-3-3)

ረሺድ ማታውሲ

መድሀኔ ብርሀኔ – ኤፍሬም ጌታቸው – ክዌኪ አንዶህ – ኄኖክ መርሹ

አብርሀም ታምራት – የአብስራ ተስፋዬ

እንዳለ ከበደ – ዓለምአንተ ካሳ – አቤል እንዳለ

አኩዌር ቻሞ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *