የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልዋሎ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የመቐለው ትግራይ ስታድየም ላይ የተደረገው የወልዋሎ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በፈረሰኞቹ 1-0 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል። 

“ዋንጫውን ካላነሳነው ቀጣይ ዓመት እዚ አታዩኝም” ስቴዋርት ሃል – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው

” ጨዋታው ተቀራራቢ ነበር። እኛም እነሱም በተመሳሳይ በተቃራኒ የማ አጋማሽ ላይ ለመጫወት እንሞክር ነበር። ሁለታችንም በተመሳሳይ ከኳስ ቁጥጥር በተሻለ መልሶ ማጥቃት ጥሩ ነበርን። እነሱም እኛም በተመሳሳይ ኳስ ተቆጣጥረን ስናጠቃ ተከላካይ ክፍልን ሰብረን መግባት ተቸግረን ነበር። በአጠቃላይ ሁለታችንም በመልሶ ማጥቃት ላይ ጥሩ ነበርን።

” ጠንካራ ጨዋታ ነበር፤ በርግጥ ሁሉም የሜዳ ውጪ ጨዋታ ከባድ ነው። ባለፈው ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫውን ያጣበት ምክንያት የጎል ልዩነቱ ጥቂት በመሆኑ ነበር። ቡድኑም ከሜዳ ውጭ ለማሸነፍ ይቸገር ነበር። በዚህ ዓመት እነዚህ ሁለት ነገሮችን ለመፍታት ነበር ያቀድነው ። ከወዲሁ ሁለት ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎችን አሸንፈናል። ከዚ ውጭ ጥሩ የግብ ክፍያ አለን። በዚ ምክንያት በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ያቀድናቸውን ነገሮች እያሳካን ነው። ”

ስለ ሜዳው ድባብ 

” እንደ ሜዳችን ነበር። የጨዋታው ድባብ በጣም ጥሩ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ለደገፉን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለው። ”

ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጉዞ

” ዋንጫውን ካላነሳነው ቀጣይ ዓመት እዚህ አታዩኝም። ዋንጫውን ለደጋፊዎቻችን ለተጫዋቾቼ እና ለአጠቃላይ የቡድኑ አባላት አስረክቤ ከቡድኑ ጋር ለቀጣይ ዓመታት ለመቆየት ነው ፍላጎቴ። በቃ እግር ኳስ እንዲህ ነው፤ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉ ክለቦች ሁለተኛ መሆን አይገባቸውም።”


“እንደ ነበረው ፉክክር ውጤቱን እንዲህ አልጠበኩትም” ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም – ወልዋሎ

ስለ ጨዋታው

ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳያችሁት ጥሩ ቅርፅ ይዟል። በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ ጥሩ የማሸነፍ መንፈስ የያዘ ቡድን ነው። በዚህ ምክንያት ጠንካራ ቡድን እንደሆነ ገምተን ጠንክረን ለመግባት ሞክረናል። ወደ ጨዋታው ስንገባ ሁለታችንም ሙከራዎች አድርገን ነበር። ልዩነቱ የልምድ ነበር፤ በተለይም ሶስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ የነበራቸው እንቅስቃሴ ይህን ያሳያል። መሐል ሜዳ ላይ ጫና ፈጥረው የቀሙን ኳስ ግብ በመልሶ ማጥቃት አስቆስጥረውብናል።

” እንደ ነበረው ፉክክር ውጤቱ እንዲ አልጠበኩትም ነበር። በርካታ ሙከራዎች አድርገናል። ውጤቱን በፀጋ ተቀብለን ብዙ መስራት ያለንን ነገሮች አይተናል። ትልቁ ችግራችን የቡድናችን ጥበት ነው፤ አማራጭ አጥተናል። ሶስት የመሃል ተጫዋቾች ነው ያሉን፤ አዶንጎም ጉዳት ላይ ነበር። ልምምድ ሳይሰራ ነው ወደ ጨዋታ የገባው። ከዚ ውጭ ፈጣሪ ተጫዋቾቻችን አፈወርቅ እና ዋለልኝ ሁለቱም በአንዴ ማጣታችን ጎድቶናል።

” ተጫዋቾቻችን ቡድናችን አሸንፎ እንዲወጣ እያረጉት ያሉት ጥረት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በዚ አጋጣሚ ተጫዋቾቼን ማመስገን እፈልጋለው።

ቡድናቸው ላይ ያለው የአማራጭ ጥበት 

የገባብን ጎል እና ያገባነው ጎል ሁለቱም በተመሳይይ ጥቂት ነው። ማግባት ላይ ያሉንን ችግሮች ለመቅረፍም አንድ ተጫዋች እያመጣን ነው። በዓመቱ መጀመርያ ላይ የቡድን ጥበት እና የጥራት ችግር ላይኖርህ ይችላል። ውድድር ከጀመርን በኋላ ግን ብዙ ችግሮች አጋጥመውናል። ዓመቱ ሲጀመር በዚ ሊግ ከታዩት ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ዳዊት ፍቃዱን እና ሌሎችን አምጥተን ነበር የጀመርነው። ከዛ በትግራይ ዋንጫ ዳዊት ተጎዳብን። ቆይቶም ጉዳት ስላስተናገደ በዚ ሰዓት በመጨረሻው ምዕራፍ ደርሰናል። አንዳንዶቹን በተደጋጋሚ ጉዳት አንዳንዶቹም በቅጣት ስታጣ ትቸግራለህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *