የአስመራው ውድድር ላይ የጊዜ ለውጥ ተደረገ

በየካቲት ወር ላይ በአስመራ ሊካሄድ የነበረው የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ በሁለት ወር መራዘሙ ታውቋል።

ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ወጣት ቡድኖች የሚሳተፉበትና ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደው ‘የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ’ በአስመራ ከተማ ይካሄዳል። በዚህ የአራቱን አባል ሃገራት ወዳጅነት እና የዞኑን የእግርኳስ ትስስር ለማጠናከር ታስቦ በሚካ ደው ይህ ውድድር የካቲት ስምንት ጀምሮ እንደሚካሄድ መግለፃችን ይታወቃል።

አሁን ከኤርትራ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተገኘው መረጃ መሰረት ከየካቲት ወር ሊካሄድ የታሰበው ውድድር ወደ ሚያዚያ መሻገሩን ሰምተናል። የጊዜ ለውጥ የተደረገበት ምክንያት የተገለፀ ባይሆንም ከሚያዚያ 4 – 12 ድረስ እንደሚካሄድ ግን ታውቋል። ይህንን ለተሳታፊ ሀገሮች በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ለማወቅ ችለናል።

በመጨረሻም የጊዜው ለውጥ የተደረገበት ቀን ከላይ የጠቀስነው ይሁን እንጂ ወደ ፊት የሚቀየር አዳዲስ ነገሮች ካሉ የምናሳውቅ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *