የከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር መቼ እንደሚጀምር ታውቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች መቼ እንደሚጀምሩ ከውሳኔ ላይ ደርሷል።
በምድብ ሀ ሙሉ ለሙሉ፣ በምድብ ለ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እንዲሁም በምድብ ሐ አንድ ሳምንት እና ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚቀሩ ሲሆን መጋቢት አንድ ላይ ሁሉም የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ የምድብ ሀ እና ለ መጋቢት 14 እና 15፤ የምድብ ሐ ደግሞ በአንድ በሳምንት ዘግይቶ የሁለተኛው ዙር ይጀምራል ተብሏል።

አምና ነሀሴ 30 የተጠናቀቀው ውድድር ዘንድሮ በሶስት ምድብ ከመከፈሉ እና አብዛኛዎቹ ጨዋታዎች መርሐ ግብራቸውን ጠብቀው እየተካሄዱ እንደመሆናቸው ክረምት ከመግባቱ በፊት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ (12ኛ ሳምንት) ጨዋታዎች

ምድብ ሀ
ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2011
አውስኮድ ከ ፌደራል ፖሊስ

እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2011
አክሱም ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ወሎ ኮምቦልቻ ከ ሰበታ ከተማ
ወልዲያ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ገላን ከተማ
ደሴ ከተማ ከ ቡራዩ ከተማ

ምድብ ለ
እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2011
ሀምበሪች ከ ኢኮስኮ
ሀላባ ከተማ ከ ናሽናል ሴሜንት
ወላይታ ሶዶ ከ ዲላ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ
የካ ክፍለ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ
ኢትዮጵያ መድን ከ ነጌሌ አርሲ

ምድብ ሐ
ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2011
ጅማ አባቡና ከ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ

እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2011

ካፋ ቡና ከ ሻሸመኔ ከተማ
ቡታጅራ ከተማ ከ ነገሌ ቦረና
ቤንች ማጅ ቡና ከ ነቀምት ከተማ
ስልጤ ወራቤ ከ ሀዲያ ሆስዕና
አርባምንጭ ከተማ ከ ከንባታ ሺንሺቾ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *