ከፍተኛ ሊግ | የጅማ አባቡና ተጫዋቾች ልምምድ አቁመዋል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ተመድቦ እየተወዳደረ የሚገኘው የጅማ አባቡና ተጫዋቾች ያለፉትን አራት ወራት ደምወዝ ስላልተከፈላቸው ዛሬ ጠዋት መስራት የነበረባቸውን ልምምድ አለመስራታቸው ታውቋል።

ተጫቾቹ ጥያቄ ማቅረብ የጀመሩት ካለፈው ወር ጀምረው ቢሆንም ጥያቄያቸውን ቀርቦ ሊረዳና መፍትሔ ሊሰጥ የሚችል አካል ባለመኖሩ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ማስገባታቸውን በመግለፅ ልምምድ ለማቆም እንደተገደዱ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ካለፈው ዓመት ጀምሮ የክለቡ ህልውና አጠያያቂ ደረጃ ላይ መድረሱ በተደጋጋሚ የታየ ሲሆን ባሰለፍነው ሳምንት በተስተካይ ጨዋታ ቡታጅራን ከመመራት ተነስተው 2-1 ባሸነፉበት ጨዋታ ግብ ያስቆጠረው ካርሎስ ዳምጠው ግብ ካስቆጠረ በኃላ በውስጥ ቲሸርቱ ላይ “ኑ አባቡናን እንታደግ” የሚል መልእክት ማስተላለፉ ክለቡ መንታ መንገድ ላይ መቆሙን የሚያመለክት ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *