ከረጅም ወራት የጉልበት ጉዳት በኋላ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በጥሩ ብቃት የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ የቀዶ ጥገና አደረገ።
ከረጅም ወራት ጉዳት በኃላ ዳግም ወደ ሜዳ የተመለሰው የፈረሰኞቹ የፊት አጥቂ ከቡድኑ ጋር ወደ ባህርዳር ለማቅናት የመጨረሻ ልምምዱን እየሰራ ባለበት ወቅት ነበር የውስጥ ህመም እንደተሰማው በመግለፅ ልምምድ አቋርጦ የወጣው። ወደ ሆስፒታልም ካመራ በኋላም የትርፍ አንጀት ህመም እንደሆነ ተነግሮት ቅዳሜ ረፋድ ላይ የተሳካ የቀዶ ጥገና በማድረግ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በኋላ ከሜዳ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚርቅ የህክምና ባለሙያዎች በሚነግሩት ውጤት መሰረት እንደሚታወቅም ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
ሳላዲን ሰዒድ እስካሁን በሊጉ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ከአቤል ያለው ጋር በጥምረት የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡