በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ማጣርያ ማሊን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን 1-1 ከተለያየ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል።
“በዛሬው ጨዋታ ባየሁት ነገር ተደስቻለሁ” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ
ዛሬ የገጠምነው በምዕራብ አፍሪካ ጠንካራ ከሚባለው ቡድን ጋር እንደመሆኑ በዛሬው የጨዋታ እንቅስቃሴ በጣም ተደስቻለሁ። በግብ ሙከራ፣ በኳስ ቁጥጥር እንዲሁም በእንቅስቃሴ የኛ ቡድን ብልጫ ነበረው።
ከሰሞኑ የወዳጅነት ጨዋታ እና የልምምድ አኳያ ሁለት የተለያዩ እቅዶች ላይ መሰረት አድርገን ነበር የተጫወት ነው። ሙሉ ቡድኑ የተሰጠውን ታክቲክ ተገብርውታል ማለት ባልችልም ልጆቼ የሚችሉትን ያህል ሞክረዋል። በተለይ የተከላካይ ክፍላችን ከገባበት ግብ ውጭ ሙሉ ለሙሉ ተግብሮታል።
ከተቀየሩት ተጫዋቹች ውስጥ አፈወርቅ ኃይሉ የተሰጠውን ሚና በትክክል ተውጥቷል። አፈወርቅ ይህ የመጀመሪያው ኢንተርናሽናል ጨዋታው ነው። እንዲህ አይነት ተጫዋቾች ልምድ እያዳበሩ ሲመጡ ብሄራዊ ቡድኑ ጠንካራ ይሆናል።
ከነዓን ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ በሁለተኛ አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጓል። ከፊት ካሉት ጋር ጥሩ ይናበብ ነበር። በቀጣይ ጠንክረን የምንሰራበት ይህ ቦታ ነው። የመሐሉ እና የፊቱ ላይ መስራት አለብን።
እኛ ላይ ያለው ችግር የአጨራረስ ነው። ይህንን ጠንክረን እንሰራበታለን። አማኑኤል እያመመው ሲጫወት እያወራሁት ነበር። የመጨረስ ፍላጉት ስለነበረው ነው ሜዳ ላይ ያቆየሁት። በቆይታውም ጥሩ ነገሮችን ሰርቷል።
በቀጣይ ወደ ማሊ ስናመራ ይህን ውጤት መቀልበስ እንደምንችል በሙሉ ልብ ነው። ሥነ-ልቡና ላይ እንሰራለን። የተወሰነ የታክቲክ ለውጥም እናደርጋለን። ባለችን አጭር ጊዜ ውስጥ ያሉብንን ክፍተት አስተካክለን ውጤት ማስመዝገብ እንደምችል አምናለሁ።
የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia
“አሁንማ አልፈናል፤ ከዚህ በኋላ ምን ትጠብቃላችሁ” የማሊ አሰልጣኝ ፋኝዬሪ ዲያራ
ማክሰኞ ሊጫወቱ አስበው ስለነበረው የወዳጅነት ጨዋታ
ማክሰኞ ዕለት የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ አልተጫወትንም። በርግጥ ሁሌም ልምምድ ስናደርግ የነበረው ቅዳሜ እንደምንጫወት በማሰብ ነበር፡፡ የጨዋታውን መቀየር ያወቅነው። ማክሰኞ ዕለት የወዳጅነት ጨዋታ ልናደርግ እየተዘጋጀን ባለበት ሁኔታ የጨዋታው ቀን ወደ ሐሙስ መቀየሩን ስናውቅ ሰርዘን ወደ ኢትዮጵያ መጣን፡፡
ስለ ጨዋታው
ሁለት የተለያዩ ግማሽ ጨዋታዎችን ነው ያየነው። የመጀመሪያውን ግማሽ እኛ ጥሩ ነበርን፤ ሁለተኛውን ደግሞ ኢትዮጵያ፡፡ በርግጥ እኛ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነው ጨዋታውን ያደረግነው፡፡ የገባነው ትናንትና ማታ ከምሽቱ 4 ሰዓት ነው ኤርፖርቱን ስንለቅ በጣም መሽቷል። 3 ተጫዋቾች ዛሬ ነው የገቡት። በቂ የማገገሚያ ጊዜ አልነበረንም፡፡
ስለ አየሩ እና ሜዳው
በከፍተኛ አልቲቲዩድ ተጉዘን ነው የመጣነው፡፡ በጣም ከመሸ ነው አዲስ አበባ የገባነው። በቂ የእረፍት ጊዜ አልነበረንም። ለዛም ነው ሁለተኛው ግማሽ የከበደን። የሜዳውም አስቸጋሪነት መናገር ያስፈለጋል። ሜዳው በጣም አስቸግሮናል። በጣም አስቀያሚ ሜዳ ነው፡፡
ስለ ውጤቱ
አሁንማ አልፈናል። ከዚህ በኋላ ምን ትጠብቃላችሁ፤ በሜዳችሁ ማሸነፍ ነበረባችሁ። ነገር ግን አላሸነፋችሁም። አሁን ደግሞ የኛ ተራ ነው። በሜዳችን አሸንፈን እናልፋለን፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡