ሰማያዊዎቹ ባለፈው ሳምንት በራሱ ፍቃድ በለቀቀው መለሰ ጋብር ምትክ ታደሰ አብርሃን በምክትል አሰልጣኝነት ቦታ ተክተዋል።
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሃየን በመቅጠር በርካታ ተጫዋቾች በማሰነበት በምትካቸው ተጫዋቾች በማስፈረም ሁለተኛውን ዙር የጀመሩት ደደቢቶች አሁን ደሞ ባለፉት ዓመታት በክለቡ የታዳጊ ቡድን እና የሴቶች ቡድን በተለያዩ ቦታዎችን ያገለገለውን እና ባለፈው ሳምንት በራሱ ፍቃድ ከስራው በለቀቀው ወጣቱ አሰልጣኝ መለሰ ጋብር ምትክ ታደሰ አብርሃን በምክትል አሰልጣኝነት ቀጥረዋል።
ባለፈው ሳምንት በግል ጉዳይ ምክንያት በራሱ ፍቃድ ከስራው የለቀቀው መለስ ጋብር ባለፉት ዓመታት በደደቢት ሴቶች ቡድን እና ወጣት ቡድን ከማገልገሉም በተጨማሪ በዚህ ዓመት ወደ ዋናው ቡድን አሰልጣኞች ቡድን ተቀላቅሎ የጌቱ ተሾመ እና ኤልያስ ኢብራሂም ምክትል ሆኖ መስራቱ ይታወሳል።
በዓመቱ መጀመርያ የወልዋሎ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን ተሹሞ ቡድኑን በመጀመርያው ዙር ያገለገለው የቀድሞ የጉና ንግድ ግብ ጠባቂ ታደሰ አብርሃ ባለፈው ወር መጨረሻ ከወልዋሎ ጋር ከተለያየ በኃላ ብዙም ሳይቆይ ወደ ሌላው የትግራይ ክለብ ደደቢት ተዘዋውሯል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡