በአሁኑ ወቅት በእጅጉኑ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ የዓለም ህዝብ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመካለከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ከአጋር ድርጅቶቹ ሞሀ ለስላሳ መጠጦች እና ከደርባ ሲሚንቶ ጋር በመሆን ወረርሽኙን ለመካለከል እንዲረዳ 5 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ሊለግስ ነው።
የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብነት ገብረ መስቀል ለምንግዜም ጊዮርጊስ ራዲዮ ማምሻውን እንደተናገሩት የህክምና ቁሳቁሱን ነገ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚያስረክብ ገልፀው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት በሚሰማው ሁኔታ ራሱን እና ቤተሰቡን ከዚህ አስከፊ በሽታ አንዲጠብቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ይህን ወረረሽኝ ለመቆጣጠር በስፖርቱ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማቶች ድጋፍ ማድረጋቸው እየተነገረ መሆኑ መልካም ዜና ሲሆን በቀጣይ መሰል ድጋፎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ መልዕክታችን ነው።
© ሶከር ኢትዮጵያ