የሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋቾች ጥያቄ መመለስ ጀምሯል

የደመወዝ ክፍያ እና የአምና ተጫዋቾች የሽልማት ይከናወንልን ጥያቄ በከፊል መመለሱ ተገለፀ።

ከሁለት እስከ አራት ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው ቆይተው የነበሩ ተጫዋቾች ዛሬ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት የሁለት ወራት ደመወዝ ተፈፅሞልናል ያሉ ሲሆን ቀሪውን ሙሉ ክፍያ ግን በዚህ ወር መጨረሻ ክለቡ እንደሚከፍለን ተግባብተናል ብለዋል ክለቡም ቀሪ የሁለት እና የአንዳንድ ተጫዋቾችን የሶስት ወር ክፍያ በወሩ መጨረሻ ከፍዬ አጠናቅቃለሁ የሚል ምላሽን ሰጥተውናል፡፡

ሁለተኛ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረው ጉዳይ ዐምና በከፍተኛ ሊግ በክለቡ ሲጫወቱ የነበሩ ተጫዋቾች ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የመሬት ሽልማት ነበረን እስከ አሁን አልተፈፀመልንም በማለት ቅሬታን ሲያቀርቡ የከረሙ ሲሆን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ እንደገለፁልን ከሆነ ይህን ችግር ለመቅረፍ የካርታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ እና ከክለቡ ቦርድ ጋር በቅርቡ በመነጋገር ተፈፃሚ እንደሚያደርጉ ገልፀውልናል፡፡

የሜዳ ዕድሳትን ማከናወን ከጀመረ ወር ያስቆጠረው ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ የሚያደርግበትን የአብዮ ኤርሳሞ የሳር ማንጠፍ ስራን እየከወነ ይገኛል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ