የከፍተኛ ሊጉ ክለብ መከላከያ ከዋና አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራው ጋር መለያየቱ ታውቋል።
ወደ ከፍተኛ ሊጉ ወርዶ ውድድሩ እስከተሰረዘበት ወቅት ድረስ በምድብ ለ እየተወዳደረ የነበረው መከላከያ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በዚህም የሥራ አመራር ቦርዱ ከአሰልጣኝ ዘላለም ጋር ለመለያየት ከውሳኔ ላይ ደርሷል። አሰልጣኙ በክለቡ ለመቆየት ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም በክለቡ ውሳኔ መሰረት መልቀቂያቸውን መውሰዳቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
የተለያዩ አሰልጣኞችን እየተመለከተ የሚገኘው ጦሩ በቀጣይ ቀናት አዲሱ አሰልጣኝን በይፋ እንደሚቀጥር ይጠበቃል።
በኮሮና ምክንያት በተሰረዘው የዘንድሮ የከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ ራሱን በተጫዋች አጠናክሮ የቀረበው መከላከያ ከ11 ጨዋታ አንድ ሽንፈት ብቻ ቢያስተናግድም የምድቡን ከፍተኛ የአቻ ውጤቶች (6 አቻ) በማስመዝገብ ከመሪው ያለው ልዩነት በመስፋቱ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት አስቸጋሪ አድርጎበት እንደነበር ይታወሳል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ