ፋሲል የተጫዋቾቹን ውል ማደሱን ሲቀጥል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተቃርቧል

ፋሲል ከነማ የሰዒድ ሀሰንን ውል ለማደስ ሲስማማ ይድነቃቸው ኪዳኔን የግሉ ለማድረግ ተቃርቧል።

የያሬድ ባዬ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ከድር ኩሊባሊን ውል ለማደስ የተስማሙት ዐፄዎቹ በሳምንቱ መጀመርያ ከሀብታሙ ተከስተ ጋር የተስማማ ሲሆን አሁን ደግሞ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ካደገ ጊዜ ጀምሮ ቡድኑን በወጥነት ሲያገለግል የቆየው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሰዒድ ሀሰንን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።

ከዚህ ቀደም የመስመር ተጫዋቹ ግርማ ዲሳሳን የቀላቀሉት ፋሲሎች የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል። መከላከያን በመልቀቅ በ2012 የውድድር ዘመን ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ወልቂጤ ከተማን ያገለገለው ይህ ግብ ጠባቂ የቀድሞው አሰልጣኙን ጥሪ ተከትሎ የዐፄዎቹ ሁለተኛ ፈራሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ