ወልቂጤ ከተማ አዲስ ውሳኔ ወሰነ

የ2012 አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ በቀጣይ የውድድር ዓመት በተጫዋቾች ዝውውር ዙርያ የማይጠቀምበትን አዲስ ውሳኔ አሳወቀ።

ለቀጣይ የውድድር ዘመን በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ ለመቅረብ ራሱን ከወዲሁ የአሰልጣኙን ውል በማራዘም፣ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በማምጣት በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። አሁን ደግሞ ክለቡ ከዚህ በኃላ ምንም አይነት የውጭ ሀገር ተጫዋች እንደማያስፈርም አሳውቋል። ይህን ውሳኔ ክለቡ ለመወሰን የደረሰበትን ምክንያት የምን ይሆን ብለን በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን የክለቡን ም/ፕሬዝደት አቶ አበባው አነጋግረን ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል።

” ይህን ውሳኔ ለመወሰን ያበቃው በዘንድሮ ዓመት ለሊጉ ዕንግዳ በመሆናችን የውጭ ተጫዋቾችን ተጠቅመን ነበር። ሆኖም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ከእኛ ሀገር ተጫዋቾች ጋር ሲታይ ብዙም የተለየ ነገር አላየንባቸውም። ስለዚህ ሀገሪቷ ላይ ያሉ ወጣት ተጫዋቾችን ዕድሉን ቢጠቀሙበት የተሻለ ነው ከሚል ነው ከዚህ ውሳኔ የደረስነው። አሁንም ክለቡ በወጣት ተጫዋቾች እያመነ በራሱ ቀለም የሚቀጥል ይሆናል።” ብለዋል።

ወልቂጤ በ2012 የውድድር ዘመን ጃኮ አራፋት(ቶጎ)፣ ሶሆሆ ሜንሳህ (ቶጎ)፣ ዐወል መሐመድ (ጋና)፣ ፉሴይኒ አልሀሰን(ጋና) እና አሮን አሞሀ (ከጋና) አስፈርሞ እንደነበር ይታወቃል።

በሊጉ ከዚህ ቀደም መከላከያ እና ወላይታ ድቻ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና የውጪ ተጫዋቾች ያልተጠቀሙ ክለቦች እንደነበሩ የሚታወስ ነው።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ