ኢትዮጵያውያን በውጪ | የቢንያም በላይ ቡድን አቻ ተለያይቷል

12ኛው ሳምንት የስዊድን ሰፐርታን (2ኛ ዲቪዝዮን) ዛሬ በተደረገ አንድ ጨዋታ ሲቀጥል ኢትዮጵያዊው አማካይ ቢንያም በላይ ዘጠና ደቂቃ በተጫወተበት ጨዋታ ኡሚያ በሜዳቸው ከሁለት ለባዶ መመራት ተነስተው አቻ ተለያይተዋል።

ከኦርግሬይቴ ጋር በተደረው በዚህ ጨዋታ እንግዳው ክለብ በአክረማን እና ሰዒድ አዳን ግቦች ሁለት ለባዶ መምራት ቢችልም ባለሜዳዎቹ ከመመራት ተነስተው በማዙር እና ዮኤል እምባየ አማካኝነት ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ከመሸነፍ ድነዋል።

ኡሚያዎች ባለፉት ካደረጓቸው አስር ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎች ስያሸንፉ አራት ጨዋዎች አቻ ወጥተው የተቀሩት አራት ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፈዋል የቁልቁለቱን ጉዞ ተያይዘውታል። በዚህ መሰረትም ክለቡ ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች 11 ብቻ ነጥብ ሰብስቦ በወራጅ ቀጠናው ተቀምጧል።

በክለቡ የመጀመርያ ዓመቱን ማሳለፍ የሚገኘው ቢንያም በላይ በቡድኑ ቆይታው በተከታታይ ጨዋታዎች ሙሉ ዘጠና ደቂቃ በመጫወት ላይ ሲገኝ ከአንድ ሳምንት በፊትም አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ ማመቻቸቱ ይታወሳል።

ዛሬ ተቀይሮ በመግባት ለቡድኑ ወሳኝ ግብ ያስቆጠረው ከኤርትራውያን ቤተሰቦች የተገኘው የሀያ ዓመቱ አጥቂ ዮኤል እምባየም ከሁለተኛው ቡድን ባደገበት ዓመት በቡድኑ ማልያ ሁለተኛውን ግቡን አስቆጥሯል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ