ጋናዊው የተከላካይ አማካይ ጋብሬል አህመድ ሀዋሳ ከተማን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡
ወደ ኢትዮጵያ በ2002 ክረምት ከመጣ በኃላ ለደደቢት በመጫወት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር የተዋወቀው ይህ አማካይ በሰማያዊዎቹ ቤት ቆይታው ከአሁኑ የሀዋሳ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጋር መጫወት የቻለ ሲሆን ከክለቡ ጋር የሊግ እና ጥሎማለፍ ክብሮችን አሳክቷል፡፡
ደደቢትን ከለቀቀ በኋላ ለሁለት ዓመት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በ2010 ለሀዋሳ ከተማ፣ በ2011 ለመቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም በተሰረዘው የውድድር ዓመት ለፋሲል ከነማ በመጫወት አሳልፏል፡፡ ይህ ጋናዊ በይፋ በዛሬው ዕለት ለሀዋሳ ለመጫወት የአንድ ዓመት ፊርማ ለማኖር ስምምነት አድርጓል፡፡
ሀዋሳዎች ከዚህ ቀደም ሶሆሆ ሜንሳህ እና ዘነበ ከድርን ለማስፈረም መስማማታቸው ይታወሳል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ